ዛሬ ከአሰልጣኙ ጋር የተለያየው ኢትዮጵያ መድን አዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠር ከጫፍ ደርሷል!

 

ዛሬ ከአሰልጣኝ ያሬድ ቶሌራ ጋር የተለያየው ኢትዮጵያ መድን አሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተናን ለመቅጠር ከጫፍ ደርሷል።

በርካታ ቡድኖችን ከከፍተኛ ሊግ ወደ ፕሪምየር ሊግ በማሳደግ የሚታወቀው አሰልጣኙ ሰበታ ከተማን ወደ ፕሪምየር ሊጉ ካሳደጉ በኋላ በመለያየት ለበርካታ ወራት ክለብ አልባ ሆነው የቆዩት አሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተና መከላከያ ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ፣ አዲስ አበባ ከተማ ማረፊያ ይሆናል ተብሎ ቢጠበቅም ኢትዮጵያ መድን ለመረከብ ከጫፍ መድረሳቸው ነው ተገልጿል።

የአሰልጣኙ ቅጥርም በ72 ስአታት ውስጥ ይፋ ይደረጋል ተብሎም ይጠበቃል።

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport