በክረምቱ የተጨዋቾች ዝውውር ሶምሀን በመልቀቅ አዲስ አዳጊውን አስዋንን የተቀላቀለው ዑመድ ኡኩሪ ልምምድ ላይ ባጋጠመው የጉልበት ጉዳት(cruciate ligament of the knee) ከውድድር ዓመቱ ውጪ ሊሆን ችሏል።
7 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 4 ግቦችን በማስቆጠር የክለቡ ኮከብ ግብ አግቢ መሆን የቻለው ዑመድ ኡኩሪ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ነሐሴ ወር ላይ ከኒጀር ጋር ላለበት ጨዋታ የመድረስ እድሉ ጠባብ አድርጎበታል።
አስተያየት ይስጡ