የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጪው ሳምንታት ሁለት የወዳጅነት ጨዋታ እንደሚያካሂዱ ለማወቅ ተችሏል ።
ጨዋታው መቼ እንደሚካሄድ ይፋ ባይደረገም የደቡብ ሱዳን ብሔራዊ ቡድን ከዛምቢያ ጋር በኢትዮጵያ ጨዋታቸውን እንደሚያካሂዱ ይፋ ሆኗል ።
የዛምቢያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እንዳሳወቀው በመጪው ሳምንት ቅዳሜ እና ሰኞ ከ ደቡብ ሱዳን ጋር በኢትዮጵያ ጨዋታቸውን እንደሚያካሂዱ ይፋ አድርገዋል ።
ለዚህም ይረዳቸው ዘንድ የዛምቢያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሚሉቲን ሰርጆቪች ሚቾ ስብስባቸውን ማሳወቃቸው ተገልጿል ።
የዛምቢያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እንዳሳወቀው ቅዳሜ ከ ደቡብ ሱዳን ብሔራዊ ቡድን ጋር በተጫወቱ ማግስት ከ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋር በኢትዮጵያ ጨዋታቸውን እንደሚያካሂዱ አሳውቀዋል ።
አስተያየት ይስጡ