በሀገር ዉስጥ ተጫዋቾች ብቻ በሚከናወነዉ የአፍሪካ አገራት ሻምፒዮን ሽፕ (ቻን) የኢትየጵያ ብሄራዊ ቡድን ተሳታፊ ለመሆን የመጨረሻ ጨዋታቸውን ከሱዳን ጋር የመጀመሪያው ጨዋታውን ዛረሰ በ10:00 ሰዓት በሀዋሳ ኢንተርናሽናል ስታዲየም አከናውኗል በጨዋታው 1-1 በሆነ ውጤት ተጠናቋል፡፡ በአስልጠኛ አሸናፊ በቀለ እሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጀመሪያው አጋማሽ በ4-4-2 አሰላለፍ ሲገባ ግብ ጠባቂ ጀማል ጣሰው ተከላካዮች => አብዱልከሪም መሐመድ አስቻለው ታመነ አንተነህ ተስፋዬ ደስታ ዮሀንስ አማካዮች =>ሙሉአለም መስፍን ታፈሰ ሰለሞን አዲስ ግደይ ጋዲሳ መብራቴ አጥቂዎች አብዱራህማን ሙባሪክ ፤ ጌታነህ ከበደ የገቡ ሲሆን በመጀመሪያው አጋማሽ የተሻለ እንቅስቃሴ ማድረግ ችሏል፡፡ በአንፃሩ የሱዳን ብሔራዊ ቡድን በ መልሶ ማጥቃት ሙከራ ወደ ጎል መድረስ ችለዋል፡፡
በሁለተኛው አጋማሽ ሁለት የተጫዋቾች ቅያሪ ሲያደርጉ የቀኝ መስመር ተከላካዪን አብዱልከሪም መሀመድን በመሐል ክፍል ተከላካይ አማካዩ ምንተስኖት አደነ ሲቀይሩ ሌላኛው ተጨዋች ታፈሰ ሰለሞንን በ ብሩክ ቃልቦሬ ቀይረው ወደ ሜዳ አስገብተዋል፡፡ የቡድኑን ቅርፅ በ3-5-2 ቀየረው ሁለተኛውን አጋማሽ ጀምረው ታይተዋል፡፡ በዚሁ የጨዋታ እንቅስቃሴ በሱዳን ብሔራዊ ቡድን ተደጋጋሚ የጎል ሙከራ ማድረግ ችለዋል፡፡
በ77 ደቂቃ የሰይፈዲን መክበኪክ የዋልያ ተከላካዮች በማለፍ ወደ ሳጥን ይዞ በመግባት ሱዳንን መሪ ማድረግ ሲችል፡ ከ3ደቂቃዎች በኃላ ከጌታነህ ከበደ ተሰንጥቆ ያገኘውን ኳስ አብዱረህማን ሙባሪክ ዋልያዋችን አቻ ማድርግ ችሏል በዚሁ ጨዋታው ተጠናቋል፡፡
የአሰልጣኝ አስተያየት አሸናፊ በቀለ
ዛሬ ባጠቃላይ ጨዋታው ጥሩ አልነበረም፡፡የልጆቹ ከፍተኛ የልጆቹ የማሸነፍ ፍላጎት ጨዋታውን እንዳናሸንፍ አድርጎናል፡፡
የመልቀቂያ ደብዳቤ ስለማስገባታቸው ተጠይቀው ?
–መልቀቂያውን አውነት ነው አስገብቻለሁ ::
-መልቀቂያ የማስገባትህ ምክኒያት ?ከፌዴረሽኑ ጋር ያለህ ቅሬታህ ምንድነው?
ባሁን ሰዓት ምክኒያቱን ለመናገር ፍቃደኛ አይደለሁም፡፡ በቀጣይ ግዚያት እናገራለሁ ሲሉ አጠቃለዋል፡፡


አስተያየት ይስጡ