ወልዋሎ ከሶስት ተጨዋቾቹ ጋር ለመለያየት ከስምምነት ደርሷል

 

በወቅቱ የተጨዋቾች ዝውውር ላይ አዳዲስ ተጨዋቾች በማስፈረምና በማሰናበት ላይ የተጠመዱት ወልዋሎዎች ክረምት ላይ ካስፈረምዋቸው ፍቃዱ ደነቅ፣ካርሎስ ዳምጠውና ምስጋናው ወልደዮሀንስ ጋር በስምምነት ለመለያየት ተስማምተዋል።

 

ከቢጫ ለባሾቹ ጋር ሚያቆያቸው ቀሪ ውል የነበራቸው ሶስቱ ተጨዋቾች ከክለቡ በመጣ ጥያቄ መሰረት በስምምነት ውላቸውን ሚቀዱ ይሆናል።ከዚህ ቀደም ወልዋሎዎች ከሚኪኤሌ ለማ፣ዘሪሁን ብርሀኑ፣ኬኔዲ አሽያ፣ኤርሚያስ በለጠና ብሩክ ሰሙ ጋር በስምምነት መለያየታቸው ሚታወስ ነው።