ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲ በ2012 የኢትዮጵያ ፕሪምየርሊግ ሁለገብ ተጫዋቾችን በማካተት ጥሩ አጀማመር ቢያሳይም ቡድኑ በወጥነት ለመዝለቅ ግን ሲቸገር እየተስተዋለ ይገኛል። በተለይም ቡድኑ ከሜዳ ውጭ ሙሉ ሶስት ነጥብ ይዞ ቢወጣም። በሜዳው የሚያከናውናቸው ጨዋታዎች ላይ አስፈላጊውን ነጥብ የመሰብስብ ላይ ግን ችግሮች እየታዩበት ይገኛሉ። በዚህም መሰረት ውጤቱ ላይ ተፅእኖ አላቸው የተባሉ ተጫዋቾች ማስጠንቀቂያ እንደደረሳቸው ነው ሀትሪክ ስፖርት ያገኘችው መረጃ የሚጠቁመው። ወልዋሎን ጨምሮ ሌሎች ሶስት የሊጉ ተሳታፊ ክለቦችም ለተጫዋቾቻቸው ማስጠንቀቂያ እንደሰጡ የሚታወስ ነው።
ማስጠንቀቂያ ከደረሳቸው ተጫዋቾች መካከል
ኬኔዲ አሺያ፣ኤርሚያስ በለጠ፣ዳዊት ወርቁ፣ ዘሪሁን ብርሀነ ፣ሚካኤል ለማ፣ራምኬል ሎክ፣ጠዓመ ወ/ኪሮስ፣ ክብሮም ዘርኡ፣ ስምኦን ማሩ እና ሺሻይ መዝገቦ የሚጠቀሱ ናቸው።
አስተያየት ይስጡ