ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ የአሰልጣኝ ቅጥር አውጥቷል !

 

በዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ግሩም የሚባል አጀማመርን በማሳየት የሊጉ አናት ላይ የቆዩት ወልዋሎዎች በአምስት የስራ ዘርፍ ላይ የቅጥር ማስታወቂያ አውጥተዋል ።

ሀትሪክ ስፖርት ባገኘችው  ማስረጃ ወልዋሎዎች የክለብ ስራ አስኪያጅ ፣ ቴክኒካል ዳይሬክተር ፣ የቡድን መሪ ፣ የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝን ጨምሮ በማርኬቲንግ ሀላፊነት ላይ የስራ ቅጥር ማውጣታቸውን ለማወቅ ተችሏል ።

ክለቡ እንዳሳወቀው ማስታወቂያ ከሚወጣበት ከነገው ቀን አንስቶ ባሉት ሰባት ተከታታይ የስራ ቀናት በክለቡ ጽ/ቤት ወይም በተወካይ በመገኘት ማመልከት እንደሚቻል አሳስበዋል ።

ክለቡ ያወጣው ይፋዊ የስራ ማስታወቂያ ይመልከቱ 👇

 

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor