ወልቂጤ ከተማን ወደ ፕሪምየር ሊጉ ያሳደገው ደረጄ በላይ በአዲስ ክለቡ ጌዲኦ ዲላ አዳዲስ ተጨዋቾችን በማስፈርም ላይ ይገኛል።
በከፍተኛ ሊጉ የሚወዳደሩት ጌዲኦ ዲላዎች ሰለሞን ብሩን ከወልቂጤ ከተማ ማስፈረም ችለዋል።አምና ከደረጄ በላይ ጋር በመሆን ወልቂጤ ከተማን ወደ ፕሪምየር ሊጉ ያሳደገው ሰለሞን ብሩ ለሌላ ግዳጅ ከቀድሞ አሰልጣኙ ጋር ተገናኝቷል።

ሌላኛው ከወልቂጤ ከተማ ዲላን የተቀላቀለው አማካዩ ሀምዲ ሶፊ ነው።ሀምዲ የአሰልጣኙን ደረጄ መንገድ በመከተል ጌዲኦ ዲላን ተቀላቅሏል።በተጨማሪ ጌዲኦ ዲላዎች መና በቀለን ከኢኮስኮ፣ዳንኤል ከቤንቺ ማጂ አስፈርመዋል።
በተያያዘ ዜና የመጠሪያ ስማቸውን ከዲላ ከተማ ወደ ጌዲኦ ዲላ መቀየራቸውን የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ ተዘራ ጌታሁን ለሀትሪክ ስፖርት ድህረገጽ አስታውቀዋል ።
አስተያየት ይስጡ