መነሻ ገጽ አፍሪካ ወላይታ ድቻ በዛንዚባር የመጀመሪያ ቀን ልምምዱን ትናንት  ጨዋታውን በሚያደርግበት አማኒ ስታዲየም አከናውኗል 
አፍሪካወላይታ ድቻዜናዎች

ወላይታ ድቻ በዛንዚባር የመጀመሪያ ቀን ልምምዱን ትናንት  ጨዋታውን በሚያደርግበት አማኒ ስታዲየም አከናውኗል 

አጋራ
አጋራ

በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካኘ ሀገራችንን ወክሎ እሚሳተፈው ወላይታ ድቻ በዛንዚባር በህንድ ዉቂያኖስ ዳርቻ ላይ በሚገኘዉ አብላ ቢች አፓርትመንታል  መቀመጫውን በማድረግ  የመጀመሪያ ቀን ልምምዳቸውን   ማከናወን ችለዋል ።

ቡድኑ አሰልጣኝ መሣይተፈሪን በማሰናበት ከ20 ዓመት በታች አሰልጣኙን ዘነበ ፍስሀን በሀላፊነት ከሾመ በኃላ የተሻለ መነቃቃት ማሳየት የቻለ ቡድን ሆኗል።
 ወላይታ ድቻ የመጀመሪያ የክለቡ ኢንተርናሽናል ጨዋታ ለማድረግ ሐሙስ እለት ወደ ዛንዚባር በማቅናት እሁድ ለሚደረገው ጨዋታ ከወዲሁ መዘጋጀታቸውን አሰልጣኙና የቡድኑ ተጫዋቾች ለሀትሪክ ስፖርት ድህረ-ገፅ ተናግረዋል። አያይዘውም ዛንዚባር ከተማ የአየር ሁኔታ በጣም ሞቃታማ መሆኑን በመግለፅ  በዛሬው የመጀመሪያ ቀን ልምምዳቸው ጨዋታቸውን በሚያደርጉበት አማኒ ስታዲየም  የአጨራረስ ትሬኒንጎችን ከጎል ጋር መስራት እንደቻሉ ገልዋል ። አያይዘውም ዛሬ የመጨረሻ ቀን ቀላል ልምምዳቸውን ጠዋት 4ሰዓት እንደሚያከናውኑ ተናግረዋል ።

በባህር የተከበበችውና በርካታ የውጪ ሀገር ጎብኚዎች እምታስተናገደው ዛንዚባር የአየር ሁኔታዋ  በጣም ሞቃታማ ሲሆን በከፍተኛ 31° በዝቅተኛው 24° ዲግሪሴንቲ ግሬድ መሆኑን የአለምአቀፉ የአየር ትንበያ weather.Com ድህረ ገፅ መረጃ ያመላክታል።

የሁለቱ የኮንፌዴሬሽን ተፋላሚ ክለቦች ጨዋታ ነገ በ10:00  በዛንዚባር አማኒ ስታዲየም እሚደረግ ይሆናል

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ኢትዮጵያ ቡና ግብ ጠባቂ አስፈረመ

መሳይ አያኖ አዲሱ የኢትዮጵያ ቡና የግብ ዘብ ሆኗል። በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሚሳተፈው...

ሲዳማ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የሲዳማ ቡና ቡድን መሪ ታገደ

በዮሴፍ ከፈለኝ የፕሪምየር ሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና የቡድን መሪው የቀድሞው ዳኛ ዕግድ...

ዜናዎችየዲሲፕሊን ውሳኔዎች

27ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አብዱላጢፍ ባምባ (መቐለ 70 እንደርታ) : ክለቡ ከ ወልዋሎ አዲግራት...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና የሊጉን መሪነት ሲያጠናክር ኤሌክትሪክ እና አፄዎቹም አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ሲዳማ ቡና ፣ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ እና ፋሲል...