በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ በምድብ ሀ እሚወዳደረው እክሱም ከተማ ከዋና አሰልጣኙ ሲሳይ አብርሃም ጋር በስምምነት ተለያይተዋል።
አክሱም ከተማ ከአሰልጣኙ ጋር ለመለያት እንደ ምክኒያት የተጠቀሰው ቡድኑ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ እያስመዘገበ እሚገኘው ውጤት አመርቂ አለመሆኑ ተከትሎ እንደሆነ ተጠቅሷል። ክለቡ ከአሰልጣኙ በተጨማሪ የቡድኑን ወጌሻም ከሀላፊነት ማሠናበቱ ተሰምቷል።
በቀጣይ አክሱም ከተማን ማን ይመራል ለሚለው ጥያቄ ምክትል አሰልጣኙ ልዑል በግዚያዊነት ቡድኑን እየመራ እንደሚቀጥል ታውቋል።
አክሱም ከተማ በዘጠኝ ጨዋታዎች መሰብሰብ ከሚገባው 27ነጥቦች ውስጥ አስራሁለቱን ብቻ በመሠብሠብ 4ተስተካካይ ጨዋታዎች እየቀሩት 9ኛ ደረጃ ላይ ሊቀመጥ ችሏል።
ቡድኑ በሳምንቱ መጨረሻ እሁድ በኢትየጵያ ከፍተኛ ሊግ 13ኛ ሳምንት ቡራዩ ከተማን በ9 ሰዓት በሜዳው እሚያስተናድ ይሆናል።