መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 19ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎቹ !
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 19ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎቹ !

አጋራ
አጋራ

 

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 19ኛ ሳምንት በተደረጉ ጨዋታዎች አምስት ጨዋታዎች በመሸናነፍ ሶስት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ሲጠናቀቁ 19 ጎሎች በ17 ተጫዋቾች ተቆጥረዋል። የጎሎቹ አገባብ አንድ በፍፁም ቅጣት ምት፣ አንድ በራስ ላይ እንዲሁም ቀሪዎቹ በጨዋታ የተቆጠሩ ናቸው። በሳምንቱ 31 ተጫዋቾችና የቡድን አመራሮች በቢጫ ካርድ ሲገሰፁ ሁለት ተጫዋች ቀይ ካርድ ተመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ማክሰኞ ሚያዝያ 8 2015 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

በተጫዋች ደረጃ በተላለፉ ውሳኔዎች ብሩክ ቃልቦሬ(ድሬደዋ ከተማ) እና ብዙአየሁ ሰይፉ(ወልቂጤ ከተማ) ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያሰጥ ጥፋት በመፈፀማቸው ቀይ ካርድ አይተው ከጨዋታ ሜዳ የተወገዱ 1 ጨዋታ እንዲታገዱ ሲወሰን በተጨማሪ ስንታየሁ ወለጬ(ኢትዮ ኤሌትሪክ)፣ መዝገቡ ቶላ(ለገጣፎ ለገዳዲ)፣ ፍቅረየሱስ ተ/ብርሀን(ሀዲያ ሆሳዕና)፣ ናትናኤል ዘለቀ(ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ መድሃኔ ብርሀኔ(ሃዋሳ ከተማ) እና ሙጂብ ቃሲም(ሃዋሳ ከተማ) 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ በመመልከታቸው በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገዱና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ/ እንዲከፍሉ ተወስኗል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
መቐለ 70 እንደርታዜናዎች

ገረሱ ሸመና መቐለ 70 እንደርታን ተቀላቀለ

በሊጉ ለመቆየት እየዳዱ የሚገኙት መቐለ 70 እንደርታዎች ረዳት አሰልጣኝ ሾመዋል። በኢትዮጵያ እግር...

ወላይታ ድቻዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

“የቀዶ ጥገና ህክምና ይደረግለታል” የወላይታ ድቻ ስራ አስኪያጅ አቶ ምትኩ ሐይሌ

ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም ከባድ ጉዳትን ያስተናገደው ወጣቱ ተጫዋች ቅዱስ ቂርቆስ በምን...

ኢትዮጵያን በውጪዜናዎች

በካናዳ የኢትዮጵያዊያን የባህል እና ስፖርት ሊግ በይፋ ተመሠረተ

በካናዳ የኢትዮጵያ የባህል እና ስፖርት በሚል ስያሜ ሊግ ተቋቋመ። የኢትዮጵያን ባህል ለአለም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...