የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሺን የ1ኛውን ዙር የኘሪሚዬር ሊግ አፈፃፀም ሪፖርት ዛሬ በጁፒተር ሆቴል የክለብ አመራሮች፡ጋዜጠኞችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት አቅርቧል፡፡
በሪፖርቱ ስለ ኘሪሚዬር ሊጉ ታሪካዊ ሂደት፡የተገኙ ውጤቶችና ፡ደካማና ጠንካራ ጎኖች፡ለችግሮች የተወሰዱ የመፍትሔ እርምጃዎች እና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች የቀረበ ሲሆን በመጨረሻም በፌዴሬሽኑ ስር ያሉ የኮሚቴ መዋቅሮች የራሳቸውን አፈፃፀም አቅርበው የተደረገውን ውይይት እንደሚከተለው ተመልክተነዋል፡፡
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሺን ባቀረበው ሪፖርት ስለ ኘሪሚዬር ሊጉ ይዘትና አጀማመር የዳሰሰ ሲሆን፡ሊጉ በ1990ቹ መጀመሪያ ስለመጀመሩና በዚያን ወቅት የነበሩት የተሳታፊ ክለቦች ቁጥር 12 እንደሆነና የመጀመሪያውን ታሪካዊ የሊግ ዋንጫ መብራት ሀይል ስለማንሳቱ እና እስካሁን ዋንጫውን 5ክለቦች ብቻ ማንሳታቸውም የተገለፀ ሲሆን እነሱም ቅ/ጊዬርጊስ፡ሀዋሳ ከተማ፡አትዬጵያ ቡና እና ፡ደደቢት ሲሆኑ የ201ዓ’ም 21ኛውን የሊግ ዋንጫ ማን እንደሚያነሳውም ጥያቄ ውስጥ ገብቷል???
በመቀጠልም ባለፉት 15 ሳምንታት የሊግ ጨዋታዎች:በጠንካራ ጎን:-
- ማሰታውቂያ -
1-የተመልካች ቁጥር መጨመር
2- እግር ኳስ ተጨዋቾች እየመጡ ስለመሆኑ
3-ክለቦች ለውድድሩ ትኩረት መስጠታቸው
4-የፀጥታ ሃይሎች በየሜዳዎቹ የሚያደርጉት ክትትል
5-ክለቦች ከሜዳ ገቢ ማግኘታቸው ሌሎች የተጠቀሱ ሲሆን
በደካማ ጎን
1-በአንዳንድ ስታዲዬሞች የተመልካች ቁጥር ማነስ
2-አልፎ አልፎ ተጨዋቾች የዳኞች ውሳኔን ያለመቀበል
3-የዳኝነት ስህተቶች
4-የፀጥታ ቁጥጥር መላላት
5-የውድድር ሰዓት ያለማክበር
6-አንዳንድ ሜዳዎች ለጨዋታ ምቹ አለመሆንና ሌሎችም አንኳር ነጥቦች የቀረቡ ሲሆን
በመቀጠልም ለችግሮቹ የተወሰዱ መፍትሔዎች እና የወደፊት የትኩረት አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
-የጨዋታ መርሃ ግብር እንዳይቆራረጥ ማድረግ
-የተሟላ ሜዳ በሌላቸው ክለቦች ላይ የእርምት እርምጃና ድጋፍ ማድረግ
-የተመልካች ቁጥር እንዲጨምር ክለቦችና ፌደሬሺኑ በቅንጅት መስራት
-ከቋሚ ኮሚቴዎች ጋር በትስስር መስራት የሚሉት ከተነሱት የቀጣይ አቅጣጫዎች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
በትግበራ ወቅት የተከናወኑ ስራዎች በሚል ፡በመጀመሪያው ዙር የሊግ ጨዋታዎች 480 ዳኞችና 120 ኮሚሽነሮች መሳተፋቸው፡443 ቢጫ ካርዶችና 23 ቀይ ካርዶች መመዝገባቸው በሪፖርቱ የቀረበ ቢሆንም፡በአዲስ አበባ ስታዲዬም ኢትዮጵያ ቡና በሜዳው ወልዲያ ከተማን 2ለ0 በረታበት ጨዋታ በወልዲያ በኩል በቀይ ከሜዳ የወጡ ተጨዋቾች መኖራቸው የሚታወስ ቢሆንም በሪፖርቱ አልተካተተም፡፡
ፌደሬሽኑ የአሰራር መዋቅር ውስጥ የሚገኙ የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ፡ዲሲፕሊን ኮሚቴ፡የብሄራዊ ዳኞች ኮሚቴ ሌሎችም የአፈፃፀም ሪፖርታቸውን ያቀረቡ ሲሆን የዲሲፕሊን ኮሚቴ በ15 ሳምንታት ብር 939.000.00 (ዘጠኝ መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ሺ) ብር ከቅጣት መሰብሰቡ በርካቶችን አስገርሟል፡፡
የ16ቱን ክለቦች ቁጥራዊ መረጃዎች ይጠብቁን!