የ19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሁለተኛ ቀን ውሎ ከደቂቃዎች በፊት ሲጠናቀቅ በወንዶች 10 ሺህ ሜትር የፍፃሜ ውድድር አትሌት ሰለሞን ባረጋ የ3ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል ።
አተሌት ሰለሞን ባረጋ በዓለም ሻምፒዮናው የኢትዮጵያን 4ኛ ሜዳልያ ያስመዘገበም ሲሆን ርቀቱን በ27:57.52 አጠናቋል ።
በውድድሩ አትሌት ሰለሞን ባረጋ እና አትሌት በሪሁ አረጋዊ በቡድን ስራ ውድድሩን እየመሩ ረዥም ሜትሮችን ለመጓዝ ችለዋል ።
ርቀቱ ሊጠናቀቅ 500 ሜትሮች ሲቀሩት ግን የወቅቱ የርቀቱ የክብረወሰን ባለቤት ኡጋንዳዊው ጆሽዋ ቼፕቴጊ በ27:51.42 በቀዳሚነት አጠናቋል።
- ማሰታውቂያ -
አትሌት ሰለሞን ባረጋ የ2ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀ ቢመስልም ኬንያዊው አትሌት ዳንኤል ኤቤንዮ በ27:52.60 ቀድሞት ገብቷል ።
አትሌት በሪሁ አረጋዊ በበኩሉ በ27:55.71 የ4ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል ።