መነሻ ገጽ ጥሎ ማለፍ ወላይታ ዲቻ የ2009 የኢትዮጵያ የወንዶች ጥሎ ማለፍ አሸናፊ ሆነ
ጥሎ ማለፍ

ወላይታ ዲቻ የ2009 የኢትዮጵያ የወንዶች ጥሎ ማለፍ አሸናፊ ሆነ

አጋራ
አጋራ

ወላይታ ዲቻ የ2009 ዓ.ም የኢትዮጵያ የወንዶች ጥሎ ማለፍ አሸናፊ መሆኑን አረጋግጧል።

መከላከያ ከ ወላይታ ድቻ በአዲስአበባ እስታዲየም በጥሎ ማለፍ ፍፃሜ ሲያገናኝ በመለያ ፍፁም ቅጣት ምት ወላይታ ድቻ አሸናፊ ሇኗል

ሁለቱ ቡድኖች ባደረጉት የፍጻሜ ጨዋታ መደበኛውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

 

መከላከያ የወላይታ ዲቻው ተከላካይ ሙባሪክ ሽኩር በ21 ኛው ደቂቃ በራሱ ግብ ላይ ባስቆጠራት ጎል የመጀመሪያውን አጋማሽ 1 ለ 0 እየመራ መውጣት ችሏል።

 

ከእረፍት መልስ ውጤቱን ለመቀልበስ ወደ ሜዳ የገቡት ወላይታ ድቻዎች በአላዛር ፋሲካ  የፍጹም ቅጣት ምት ጎል አቻ መሆን ችለዋል።

ከዚህ በኋላ በሁለቱም ቡድኖች መካከል ተጨማሪ ጎል ሳይቆጠር ጨዋታው በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

አሸናፊውን ለመለየትም ጨዋታው ወደ መለያ ምት አምርቷል።

አንድ ለአንድ በሆነ አቻ ውጤት በመለያየታቸው በተሰጠው የፍጹም ቅጣት ምት ለወላይታ ድቻ  ተክሉ ታፈሰ፣  አብዱልሰመድ አሊ ፣አላዛር ፋሲካ፣ ወንድወሰን ገረመው ሲያስቆጥሩ በእለቱ ጨዋታ ድንቅ የነበረው  ፈቱዲን ጀማል ፍጹም ቕጣት ምት አምክኖአል

ለመከላከያ ባዬ ገዛኸኝ እና ሳሙኤል ሳሊሶ ሲያስቆጥሩ አወል አብደላ ይድነቃቸው ኪዳኔ በመሳታቸው ወላይታ ድቻ 4 ለ 2  አሸንፏል ፡፡

 

 

ወላይታ ዲቻ በቀጣዩ አመት ኢትዮጵያን ወክሎ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ተሳታፊ መሆኑንም አረጋግጧል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ኢትዮጵያ ቡናዜናዎችጥሎ ማለፍ

ኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የጥሎ ማለፍ ውድድርን አስመልክቶ ላቀረበው ጥያቄ ምላሽ ተሰጠ

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው የ2011 ዓ.ም የጥሎ ማለፍ ውድድር...

LIVESCOREዜናዎችጥሎ ማለፍ

ወልዋሎ አዲግራት ከ ፋሲል ከነማ | የ2011 ኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ዋንጫ በቀጥታ ውጤት /LIVRSCORE/ ይከታተሉ

    የ2011 ኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ዋንጫ                     ረቡዕ  ጥር 1...

LIVESCOREመከላከያኢትዮጵያ ቡናጥሎ ማለፍ

ጥሎ ማለፍ | ኢትዮጵያ ቡና ከ መከላከያ በቀጥታ /LIVESCORE/ ይከታተሉ

የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ዋንጫ ማክሰኞ መስከረም 15 ቀን 2011 ዓ.ም 08:00' ኢትዮጵያ...