ኮትዲቯር ወደ አፍሪካ ዋንጫ ማለፏን አረጋግጣለች !
በዋልያዎቹ ምድብ የሚገኙት ዝሆኖቹ በምድቡ በመጨረሻ ደረጃ ላይ የምትገኘውን ኒጀር 3 ለ 0 በማሸነፍ ወደ አፍሪካ ዋንጫው አልፈዋል ።
• የኒጀር ብሔራዊ ቡድን በሜዳቸው የዛሬውን ጨዋታ መሸነፋቸውን ተከትሎ የነበራቸውን ጠባብ የማለፍ እድል ሳይጠቀሙበት ቀርቷል ።
• ዋልያዎቹ በቀጣይ ከ ዝሆኖቹ ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ የአቻ ውጤት ለ ካሜሮኑ የአፍሪካ ዋንጫ የሚያሳልፋቸው ይሆናል ።
• ኮትዲቯር የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፋቸውን ተከትሎ በአንድ ነጥብ ተሽለው ከዋልያዎቹ በላይ ተቀምጠዋል ።
• በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከ ኮትዲቯር ጋር በመጪው ማክሰኞ ጨዋታቸውን የሚያካሂዱ ይሆናል ።
ዝሆኖቹ በአስር ነጥብ ምድባቸውን በመምራት ከወዲሁ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል ።
• ዝሆኖቹ ከ ማዳጋስካር ባለቸው የእርስ በ እርስ ግንኙነት የበላይ ሆነው መገኘታቸው ከወዲሁ ማለፋቸውን እንዲያረጋግጡ ረድቷቸዋል ።
• የ ማዳጋስካር ብሔራዊ ቡድን የ መጨረሻ የምድብ ጨዋታ ቢያሸንፉ ከአሁኑ የኮቲዲቫር ነጥብ ጋር አንድ መሆን ቢችሉም እርስ በእርስ ተገናኝቶ ማን ብዙ አሸነፈ በሚለው የ ኮትዲቯር ብሔራዊ ቡድን አላፊ ይሆናሉ ።
Hatricksport.net