ክብሮም አፅብሃ (ቺቻሪቶ) ሰሎዳ ዓድዋን ተቀላቅሏል

በክረምቱ የተጨዋቾች መስኮት ዝውውር ላይ መቐለ 70 እንደርታን ተቀላቅሎ ከቡድኑ ጋር የግማሽ ዓመት ቆይታ ያደረገው ክብሮም አፅብሀ ( ቺቻሪቶ) በውሰት ውል ወደ ቀድሞ ክለቡ ለመመለስ ችሏል፡፡

 

ባለፈው ዓመት ሰሎዳ ዓድዋ ወደ ፍተኛ ሊግ እንዲገባ ከፍተኛ ሚና የተጫወተው ክብሮም በሊጉ በጥሩ እንቅስቃሴ የሚገኙት ሰሎዳ ዓድዋን ጥሩ ግብዓት ይሆናቸዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በመቐለ 70እንደርታ በርከተ ባሉ ጨዋታዎች ላይ የመሰለፍ እድል ያላገኘውን ክብሮም ክለቡን ለመልቀቁ ምክንያት እንደሆነ ይገመታል፡፡