መነሻ ገጽ ባህርዳር ከተማ ከደጋፊነት በዘለለ ክለቡ ለሴቶች ፕሪምየርሊግም ቢያሰፈርሟት ደስተኛ ነኝ የጣነው ሞገድ በእድሜ ትንሿ ደጋፊ አባት ሙሉሰው ታየ
ባህርዳር ከተማዜናዎች

ከደጋፊነት በዘለለ ክለቡ ለሴቶች ፕሪምየርሊግም ቢያሰፈርሟት ደስተኛ ነኝ የጣነው ሞገድ በእድሜ ትንሿ ደጋፊ አባት ሙሉሰው ታየ

አጋራ
አጋራ

ኢትዮጵያ ውስጥ በእድሜ ትንሿ ሌላኛዋ የባህር ዳር ከነማ ደጋፊ ረቂቅ ሙሉሰው ሁለተኛ አመቷ ባከበረች ማግስት የክለቡ አባል ሆናለች። ታዲያ በአንዳንድ የክልል ስታየዲዮሞች እንኳን ይህን የመሰለ ድርጊት ለመፈፀም ይቅር እና የጨዋታ ቀን መግቢያ ቲኬት እንኳን ላለመግዛት በአጥር ዘለው ሲገቡ ለስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል ምክንያት ሲሆኑ ከተስተዋለ ሰንበትበት ብለዋል። ከዚህ ቀደም ጁኒየር ሳሙኤል ለመጀመሪያ ግዜ በአራተኛ ወሩ የተመዘገ የክለቡ ደጋፊ ብላቴና ሲሆን የአብሳላት እና ሀምዛ እንድሪስ በ 5እና 6 ወር ይከተሉታል። በዛሬው ቀን ደግሞ ረቂቅ ሙሉሰው አራተኛዋ የክለቡ ተመዝጋቢ ነች። ታዲያ የሀትሪክ ስፖርቱ ሚሊዮን ኃይሌ ወደ ባህርዳር ደውሎ የረቂቅን አባት በስልክ በማነጋገር የሚከተለውን አዘጋጅቶልናል።

ረቂቅ የሰንት አመት ልጅ ነች ለክለቡ ሌላኛዋ በእድሜ ትኒሿ ደጋፊ መሆኗ ምን ተሰማህ?

ረቂቅ የሁለት አመት ልጅ ናት ሁለት አመቷን ባከበረችበት ማግስት ነው ደጋፊ ማህበሩ ጋር ሄደን ያስመዘገብናት። እንደውም እኛ ያሰብነው በተወለደችበት ቀን ለማስመዝገብ ነበር ግን በአንዳንድ ነገሮች ስላልተመቻቸልን ነው አሁን ያስመዘገብናት። ። በእድሜዋ የክለቡ ሌላኛዋ ትኒሿ ልጅ በመሆኗ በጣም ደስተኛ ነኝ።

ምን አነሳሳቹህ ቢዚህ እድሜዋ ለማስመዝገብ

እኔ የባህርዳር ልጅ ስለሆንኩኝ የባህርዳር ከተማ ደጋፊ ነኝ እናቷም ነፍሰ ጡር እያለች ስታዲዮም ይዣት እየገባው ኳስ እናይ ስለነበር በጣም ለክለቡ ፍቅር ስላለን ነው።

በቀጣይስ ብላቴናዋ የክለቡን ፍቅር ከማስተማር አኳያ ምን አስባችኋል።

እኔ ከደጋፊነት በዘለለ ክለቡ ለሴቶች ፕሪምየርሊግም ቢያሰፈርሟት ደስተኛ ነኝ። አሁን ላይ እራሱ ኳስ አጫውታታለው በግራ እግሯ ቁማ በቀኟ ስትመታ ብትመለከታት እውነቴን ነው እምልህ እንደ ህፃን ልጅ አይደለም። ወደፊት ተጫዋች እንደትሆን ከኔ የሚጠበቀውን ነገር ሁሉ አደርጋለው። በመጨረሻም ለህፃን ረቂቅ ሙሉሰው እንኳን ለሁለተኛ አመት ልደትሽ በሰላም አደረሰሽ ሲል ሀትሪክ ስፖርት መልካሙን ተመኝቶልሻል።

 

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

አዳማ ከአስር ፈረሰኞቹ ከሦስት እና ነብሮቹ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የመክፈቻ ቀን ጨዋታ አዳማ ከተማ በጎል ደምቆ ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ...

ዜናዎችየአዲስአበባ እግርኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጠዋል የተባሉት ሁለት ዳኞች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደረገ

በዮሴፍ ከፈለኝ በወልዋሎ እና ነገሌ አርሲ ጨዋታ ላይ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ ሁለት...

ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንፊፋ

ፊፋ ቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ጥሎት የነበረውን የዝውውር ዕገዳ በጊዜያዊነት አነሳ

ቅዱስ ጊዮርጊስ በአራት የቀድሞ ተጫዋቾች ቀርቦበት በነበረው ክስ በፊፋ ጥሎበት የነበረው የተጫዋቾች...

ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

ዋልያዎቹ በአሜሪካ የወዳጅነት ጨዋታን ሊያደርጉ ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ አሜሪካ ሊያመራ ነው ነገር ግን የወቅቱ የብሔራዊ ቡድኑ...