ከደቡብ ሱዳን ጋር የታሰበው የወዳጅነት ጨዋታ የመካሄድ ዕድሉ ጠቧል

ደቡብ ሱዳኖች ሜዳቸው በመቀጣቱ በካፍ ሌላ ገለልተኛ ሜዳ ምረጡ ተብለዋል የመጀመሪያ ዕቅዳቸው ኢትዮጲያ እንዲሆን ነበር ከተሳካላቸው በዚያውም የወዳጅነት ጨዋታ የማግኘት ዕድል ነበራቸው የኢትዮጲያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ግን ግጥሚያ ሊያደርጉ ያሰቡት ጨዋታ ቀን ኢትዮጲያ ከኒጀር ጋር የምትጫወትበት ቀን በመሆኑ የቀን ለውጥ እንዲያደርጉ ለውጡ ከሌለ ግን ጥሪውን እንደማይቀበል አሳውቋቸዋል።

ይህን ተከትሎ ደቡብ ሱዳኖች ፊታቸውን ወደሌላ ሀገር ማዞራቸው ተሰምቷል፡፡ በዚህ ምክንያት ከዛምቢያ አቻቸው ጋር የሚኖረው ሁለት ጨዋታ ብቻ የሚደረግ ይሆናል፡፡

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport