መነሻ ገጽ ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ ከዓለም 105ኛ ደረጃ ላለ እግር ኳስ ይሄሁሉ ግብግብ ለምን?ለመሆኑ ፌዴሬሽኑ ውስጥ ነዳጅ ተገኝቶ ይሆን?
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣብቸኛዋ ባለቀለም የስፖርት ጋዜጣ

ከዓለም 105ኛ ደረጃ ላለ እግር ኳስ ይሄሁሉ ግብግብ ለምን?ለመሆኑ ፌዴሬሽኑ ውስጥ ነዳጅ ተገኝቶ ይሆን?

አጋራ
አጋራ

ጠቅላላ ጉባኤው ሊራዘም ይችላል!!!!
በጠቅላላ ጉባኤው የመራጮችን ድምፅ
ለማግኘት ገንዘብ እየተረጨ ነው​
በይስሀቅ በላይ 

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ 
ጉባኤና የፕሬዝዳንትና የስራ አስፈፃሚ ኮማቴ 
አባላት ምርጫ በተያዘለት ቀነ ገደብ መካሄዱ 
አጠራጣሪ ሆኗል፡፡ 
ቀደም ሲል ጠቅላላ ጉባኤው በአፋርዋ 
ሰመራ ከተማ እንዲካሄድ ከተወሰነ በኋላ 
አሳማኝ ባልሆነ ምክንያት ወደ አዲስ አበባ 
እንዲዛወር ያደረገው የኢትዮጵያ እግር ኳስ 
ፌዴሬሽን በመቀጠልም እጩዎችን የማሳወቂያ 
ቀንን ከጥቅምት 15 ወደ ጥቅምት 20 /
ትናንት ሰኞ/ ያዘዋወረ ሲሆን ፕሮግራሞቹን 
ማጠፍና ማዘዋወር ልምድ የሆነው ፌደሬሽን 
አሁንም ጠቅላላ ጉባኤውን ከጥቅምት 30 ወደ 
ህዳር ወር ሳያሸጋግረው እንደማይቀር ነው 
ምንጮቻችን እየገለፁ ያሉት፡፡ 
ፌዴሬሽኑ በብዙዎች ዘንድ በጉጉት 
የሚጠብቀውን የዘንድሮን ጠቅላላ ጉባኤና 
ምርጫውን ለማዘዋር ስላሰበበት ጉዳይ በይፋ 
የተገለፀ ነገር ባይኖርም ጉባኤውን ለመታዘብ 
ይመጣሉ ተብለው የሚጠበቁት የፊፋ የምርጫ 
ታዛቢ ቡድን አባላት ስለመምጣታቸው 
እስካሁን ማረጋገጫ ባለመሰጠታቸ በሚል 
ምርጫውን ከጥቅምት 30 ወደ ህዳር 
ለመግፋት ምክንያት አድርጎ እያቀረበ እንደሆነ 
ነው የዜና ምንጮቻችን የሚጠቁመት፡፡
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ 
ጉባኤና ምርጫ ጥቅምት 30 ቀን ስለመካሄዱ 
ማረጋገጫ ባይገኝም በእጩነት ተወክለው 
የቀረቡ ሰዎች ግን የምረጡኝ ቅስቀሳ 
በተለያየ መንገድ አጠናክረው የቀጠሉ ሲሆን 
የጠቅላላ ጉባኤው አላባትን ድምፅ ለማግኘትና 
ለማባበል ከፍተኛ ገንዘብ እየተረጨ እንደሆነ 
ነው እየተሰማ ያለው፤ በተለይ በፌዴሬሽኑ 
ወንበር ላይ ለመቀመጥ የቋመጡ ከአንዳንድ 
ተሰናባቹ የስራ አስፈፃማ ኮሚቴ አባላት ጋር 
በመደራጀት ከክልልና ከክለቦች እንዲሁም 
ከማህበራት የሚወከሉ የጉባኤው አባላትን 
ድምፅ ለማግኘት በቡድን ተደራጅተው 
የማግባባትና በገንዘብ የማባባል ሰራ እየተሰራ 
እንደሆነ ነው ታማኝ የዜና ምንጮች 
የሚጠቁሙት፤ እነዚህ ከሶስትና ከአራት 
የማይበልጡ ግለሰቦች በቡድን ተደራጅተው 
የፌዴሬሽኑን ስልጣን ጨምድደው ለመያዝ 
ክፉኛ በመቋመጥ ከፍተኛ ገንዘብ በመመደብ 
በታላላቅ ሆቴሎች እየተሰባሰቡ የፌዴሬሽኑን 
ስልጣን በእጃቸው መዳፍ መጠቅለል 
በሚችሉበት ዙሪያ እየጠነሰሱ ውለው 
እንደሚድሩ የአይን እማኞች በተለይ ለሀትሪክ 
ገልፀዋል፡፡
ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ለፌዴሬሽኑ 
ፕሬዝዳንትነትና የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ 
አባልነት ለመመረጥ ከፍተኛ ግብግብና ዘመቻ 
የታየበት የዘንድሮው ምርጫ ብዙዎችን 
ያሳዘነ ሲሆን ይሄ ሁሉ ዘመቻ፣ በቡድን 
የተደራጀ እቅስቃሴና ከፍተኛ ገንዘብ መረጨቱ 
በፌዴሬሽኑ ግቢ ውሰጥ ነዳጅ ተገኝቶ 
ይሆን? አሊያስ የምትታለብ ላም አለች? 
የሚል ጥያቄ የስፖርት ቤተሰቡ በግርምት 
እንዲያነሳ እያስገደደው ነው። ከዓለም 150ኛ 
ደረጃ ላይ የሚገኝ፣ ከማደግ ይልቅ ቁልቁል 
እየተንደረደረ በመሄድ ላይ የሚገኝን እግር 
ኳስ ለመምራት ይሄ ሁሉ ትንቅንቅ መካሄዱ 
ከእግር ኳሱ በስተጀርባ ምን የተደበቀ ምስጢር 
ይኖር ይሆን? የሚል ጥያቄንም እንዲያነሱ 
እያደረጋቸው ነው፡፡
በተለይ ለምርጫው በእጩነት 
የቀረቡት ሰዎች አወካከል ግራ እንዳጋባቸዉ 
የማገልፁት አስተያየት ሰጪዎች የአገሪቱን 
ጠቅላይ ማኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ 
ላስተላለፉት የመንግስት መመሪያ ከመገዛትና 
ተግባራዊ ከማድረግ ይልቅ የግለሰብ አጀንዳ 
አስፈፃሚ መሆናቸው በእግር ኳሱ ላይ 
ለውጥ ይመጣል ብለው ተስፋ እንዳይደርጉ 
ተፅዕኖ እየፈጠረባቸው መሆኑን እየገለፁ 
ነው፡፡ እነዚህ አስተያየት ሰጪዎች መጪውን 
የእግር ኳስ ጊዜ በተስፋ አሻግረው እንዳያዩ 
ምክንያት የሆናቸውን በምሳሌ አስደግፈው 
ሲያስረዱ ከዛሬ 10 ዓመት በፊት ለእግር 
ኳሱ መንደር መደፍረስ፣ አገሪቱ ለሁለት 
ዓመት የፊፋ የቅጣት በትር እንዲያርፍባት፣ 
የአገሪቱ መልካም ገፅታም እግር ኳሱ ውስጥ 
በተፈጠረው ችግር እንዲጠይም ተዋናይ 
የነበሩ ግለሰቦችን በድጋሚ ወክለው ማቅረብ 
ለእግር ኳሱ ታስቦ ነው ወይስ ለግለሰብ? 
እንድንል አድርገናል ካሉ በኋላ አንድ ክልል 
ከመወከሉ በፊት እንዴት ይሄን ማጣራት 
ያቅታቸዋል?በማለትም ይጠይቃሉ። 
አንድን ሰው እንዴት ከአንድም ሶሰት 
ፌዴሬሽኖችን በፕሬዝዳንትነት ይመራል? 
የሚለውን አያገናዝቡም በአገሪቱ ሰው 
ጠፍቶ ነው? የሚል ጥያቄ እንደፈጠረባቸው 
ገልፀው ከዚህ ታሪካዊ ስህተት በተጨማሪ 
ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ቁልቁል መውረድ፣ 
ወደ 150ኛ ደረጃ ማስሽቆልቆል ምክንያት 
የሆኑት የተሰናባቹ ፌዴሬሽን አመራሮች 
ለተፈጠረው የእግር ኳስ ውድመት ህዝቡን 
ይቅርታ ጠይቀው ቦታውን ለሌሎች 
መልቀቅ ሲገባቸው ያለ ምንተፍረት 
በድጋሚ ከፌዴሬሽኑ ግቢ ላለመውጣት 
እጩ ሆነው መቅረባቸው ወካዮቹንም 
ተወካዮቹንም ለትዝብት እንደዳረጋቸውና 
በእነዚህ መሰረታዊ ምክንያቶችም በመፃኢው 
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ ተስፋ እንዳያደርጉ 
ተፅዕኖ እንደፈጠረባቸው ገልፀዋል፡፡
የአማራው ክልል ተወካዮች ከሆኑት 
ከአቶ ተካ አስፋውና ከአቶ ሰውነት ቢሻው 
በቀር በሌሎች ላይ የጠነከረ ቅሬታና ተቃውሞ 
እየተሰማ ባለበት በዚህ ሰአት የአማራው 
ክልል ተወካዮች የጠቅላይ ሚኒስትሩን 
መመሪያ ተግባራዊ አድርገዋል፤ ለእግር 
ኳሱም እጅግ በጣም አስፈላጊ ሰዎችን ነው 
የወከሉት በሚል ውክልናውን የሰጠው አካል 
በሚዲያውም በስፖርት ቤተሰቡም ከፍተኛ 
ውዳሴ እየቀረበለት ሲሆን እጩዎችም 
ገና ሳይመረጡ በተለይ በስፖርት ቤተሰቡ 
“እንኳን ወደ ስፖርቱ መጣችሁልን” አይነት 
አቀባበል ድጋፍ እየተቸራቸው ነው፡፡
ለዚህ ደግሞ ማረጋገጫው ባለፈው 
እሁድ ቅዱስ ጊዮርጊስና ወላይታ ዲቻ በአዲስ 
አበባ ስቴዲየም ለፍፃሜ በተጫወቱበት ዕለት 
የአማራ ክልልን በመወከል ለፕሬዝዳንትነት 
በእጩነት የቀረቡት አቶ ተካ አስፋው ወደ 
ስቴዲየም ሲገቡም ሆነ ሲወጡ ከስፖርቱ 
ቤተሰብ የታየው ስሜትና ሞራል በቂ ማሳያ 
ነው፡፡ 
አቶ ተካ አስፋው በዋናው የስቴዲየሙ 
መግቢያ ሲገቡና ሲወጡ በበርካታ ተመል 
ካቾች ከመከበባቸው በተጨማሪ “በባለፈው 
ምርጫው ያጣንህ ሰዎች ባቀነባበሩት ሴራ 
ነው፤አሁን ግን ለእግር ኳሱ በጣም ታስ 
ፈልጋለህ፤ ከጎንህ ነን በርታ አይዞህ” በሚሉ 
ስሜቶችና ሞራሎች የታጀቡ አስተያ የቶች 
ሲሰጡ ሀትሪክ በቦታው ተገኝታ አስተ 
ውላለች፡፡ ይህ የስፖርት ቤተሰቡ ሞራልና 
ድጋፍ አቶ ተካ አስፋው ፌዴሬሽኑ ውስጥ 
በነበሩበት ጊዜ ሰርተውት በነበረው መልካም 
ስራና ለእግር ኳሱ የዋሉት ውለታ ተቆጥሮ 
እንደሆነ ከሚዲያውና ከተመልካቹ ከሚሰጠው 
አስተያየት መረዳት ያህል ከባድ አይሆንም፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜና እረፍትዜናዎች

የጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ አጭር የህይወት ታሪክ

ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ከእናቱ ከወ/ሮ ጌጤ ገ/ስላሴ እና ከአባቱ ሀምሳ አለቃ ወልዴ...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜናዎች

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...