መነሻ ገጽ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከሄኖክ አወቀ ጋር የተለያየው ፋሲል ከተማ 3 ተጫዋቾችን ከተስፋ ቡድኑ አሳድጓል
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግፋሲል ከተማ

ከሄኖክ አወቀ ጋር የተለያየው ፋሲል ከተማ 3 ተጫዋቾችን ከተስፋ ቡድኑ አሳድጓል

አጋራ
አጋራ

በ2009 ዓ/ም ከተስፋ ቡድን ያደገው ተጨዋቾች ሄኖክ አወቀ በፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ  እስከ ሰኔ 2010
 ዓ/ም ከክለቡ ጋር የሚያቆየው ውል ቢኖርም ከክለቡ ጋር በስምምነት ውሉን በማቋረጥ ተለያይቷል፡፡

ሄኖክ አወቀ ከክለቡ ጋር  በተደጋጋሚ በደሞዝ ጭማሪና በውል ማደስ ዙሪያ በተደጋጋሚ ከክለቡ ስራ አስፈፃሚዎች ጋር ለረዥም ጊዜ የቆየ ድርድር በማድረግ  ክለቡ ለወደፊት ይጠቅመኛል በማለት  ለ2 አመት በሚያቆይ ውል 1.2 ሚሊየን ብር ቢያቀርብለትም ተጨዋቹ ባለመስማማቱ  የመልቀቂያ ጥያቄውን ለክለቡ በፃፈው ደብዳቤ አሳውቋል።
የሄኖክ አወቀን የልቀቁኝ ደብዳቤ የተመለከቱት የክለቡ ስራ አስፈፃሚዎችና የክለቡ አሰልጣኝ ምንተስኖት ጌጡ ተጨዋቹ በክለቡ መቆየት የማይፈልግ ከሆነ በጠየቀው መሰረት በስምምነት ውላቸውን በማቋረጥ ተለያይተዋል፡፡
የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብም ያለበትን የተጫዋቾች ክፍተት ለመሙላት  ፊቱን ወደ ታዳጊዎች በማዞር በአማራ ሊግ በመወዳደር ላይ ከሚገኘው የክለቡ ተስፋ ቡድን ተስፋ ሰጭ እንቅስቃሴ ያሳዩትን 3 ተጨዋቾች ወደ ዋናው ቡድን አሳድጓል፡፡

 አሰልጣኝ ምንተስኖት ጌጡ በቀጣይ ቡድናቸውን ለማጠናከር ሁነኛ ካሏቸው ተስፈኛ ታዳጊዬች የመሀል ተከላካይ ዳንኤል ዘመዴ፡የአጥቂ አማካኝ ናትናኤል ወርቁንና፡ በአጥቂ ቦታ ያሬድ አበበን ወደ ዋናው ቡድን ሲያሳድጉ በቀጣይም ተጨዋቾችን ከውጭ ሀገር ከማስመጣት ይልቅ ታዳጊዬች ላይ ትኩረት እንደሚያደርጉ ገልፀዋል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሲዳማ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የሲዳማ ቡና ቡድን መሪ ታገደ

በዮሴፍ ከፈለኝ የፕሪምየር ሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና የቡድን መሪው የቀድሞው ዳኛ ዕግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና የሊጉን መሪነት ሲያጠናክር ኤሌክትሪክ እና አፄዎቹም አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ሲዳማ ቡና ፣ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ እና ፋሲል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...