በታሪክ ለመጀመሪያ ቅዱስ ጊዮርጊስ በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ምድብ ድልድል በገባበት ባሳለፍነው አመት 7 ጎሎችን በማስቆጠር ትልቅ ሚና የነበረው የዋሊያዎቹና የቅዱስ ጊዮርጊስ የፊት መስመር ተሰላፊው ሳላሃዲን ሰይድ በምድብ ጨዋታ ከቱኒዚያው ኤስፔራንስ ደ ቱኒዝ ጋር ባደረገጉት ጨዋታ ጉዳት ማስተናገዱ የሚታወስ ነበር።
በዚሁ ጉዳት ከልምምድና ከጨዋታ የራቀው ሳላሃዲን ሰይድ በቅርቡ ወደ ልምምድ ተመልሶ ክለቡ ቅዱስ ጊዮርጊስ በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ከኬሲሲኤ ጋር የመጀመሪያ ጨዋታውን በሜዳው እና በደጋፊው አዲስ አበባ ስታዲየም ሲያደርግ ከ8 ወራት ጉዳት በኋላ ወደ ጨዋታ ተመልሶ በተጫዎተበት ዕለት ጉዳቱ በድጋሚ አገርሽቶ ወደ ውጭ ሂዶ መታከምን የሚጠይቅ በመሆኑ ፈረሰኞቹ ወደ ዩጋንዳ ለመልሱ ጨዋታ ሲያቀኑ ሳላ ለህክምና ወደ ጀርመን መሄዱ ይታወቃል፡፡
በጀርመኗ ሙኒክ ከተማ በሚገኝ ሆስፒታል የቀዶ ጥገና ህክምናውን በተሳካ ሁኔታ ማድረጉን በኢንስታግራም ገፁ ይፋ ያደረገው ሳላሃዲን ሰይድ የህክምና ክትትሉን በቅርብ አጠናቆ ወደ ሀገሩ እንደሚመለስ ገልጿል።
አስተያየት ይስጡ