ኢትዮ ኤሌክትሪኮች ግማሽ ሚሊየን ብር ለመርዳት ተስማሙ

 

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት
ኢትዮ.ኤሌክትሪክ የስፖርት ክለብ ተቀላቅሏል፡፡ ራሳቸውን ከሃላፊነት ያነሱትን የቀድሞ የክለቡ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ኢሳያስ ደንድርን ለሳምንታት ወደቦታ የመለሠው ክለቡ 500ሺ ብር ለኮሮና መከላከል እንዲውል ተስማምቷል፡፡ በዚህም መሠረት ስፖርተኞቹ 240 ሺ ብር ክለቡ ደግሞ 260ሺህ ብር ለመስጠት መስማማታቸውን ከክለቡ የተገኘ መረጃ ያስረዳል፡፡

ኢትዮ ኤሌክትሪክ በስሩ አራት የስፖርት አይነቶችን ያቀፈ ሲሆን በእግር ኳስ 6 ቡድን ሲኖረው በአትሌቲክስ 131 በብስክሌት 13 በጠረጴዛ ቴኒስ 28 በአጠቃላይ 331 ስፖርተኞችና የቡድን አባላትን መያዙ ታውቋል፡፡ ስፖርት ክለቡ የግማሽ ሚሊየን ብር ቼኩን የፊታችን ሃሙስ ወይም አርብ ለክቡር ከንቲባው ታከለ ኡማ ያስረክባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport