ኢትዮጵያ ቡና ባህር ዳር ከተማን 4ለ1 በማሸነፍ የአዲስ አበባ ዋንጫ አሸናፊ ሆነ፡፡
ዛሬ በአዲስ አበባ በተካሄደው 13ኛው የአዲስ አበባ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ የተገናኙት ኢትዮጵያ ቡና ና ባህር ዳር ከተማ ነበሩ፡፡
የፍጻሜ ጨዋታውን ኢትዮጵያ ቡና ከእረፍት በፊት ባስቆጠሩት ሶስት ጎሎችና ከእረፍት መልስ ባስቆጠሩት አንድ ጎል ታግዘው 4 ለ 1 በሆነ ውጤት የፍጻሜ ጨዋታውን በበላይነት አጠናቋል፡፡
ለኢትዮጵያ ቡና አሸናፊነት ካሉሽያ አልአሰንና በጨዋታ አምበሉ ሳምሶን ጥላሁን በፍፁም ቅጣት ምት አቡበከር ናስር ደግሞ አንድ በፍፁም ቅጣት አንድ በጨዋታ ጎሉቹን አስቆጥረዋል ፡፡

ለባህር ዳር ከተማ ከሽንፈት ያልዳኑበትን ጎል ተቀይሮ የገባው እንዳለ ደባልቄ ከእረፍት መልስ አስቆጥሯል፡፤
የፍጻሜ ጨዋታውን ኢንተርናሸናል ዳኛ በአምላክ ተሰማ የመሩት ሲሆን በርካታ የሁለቱ ቡድን ደጋፊዎች ጨዋታውን ተከታትለውታል፡፡ ለጨዋታውም ከፍተኛ ድምቀት ሰጥተውታል
የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አቶ ታከለ ኡማ እና የባህርዳር ከንቲባ አቶ ሙሉቀን አየነው በክብር እንግድነት በመገኘት ጨዋታውን ተከታትለዋል፡፡
በጨዋታው ኢንተርናሽናል ዳኛ በአምላክ የፍጹም ቅጣት ምት ለተቃወሙ አራት የባህር ዳር ተጨዋቾች ቢጫ ካርድ አሳይተዋል፡፡
አሰልጣኝ ፓውሎስ ጌታቸው ከእረፍት መልስ በኢንተርናሽናል ዳኛ በአምላክ ተሰማ ከሜዳ እንዲወጣም ተደርጓል፡፡
በሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና የተሻለ እንቅስቃሴና የጎል ሙከራዎችን ማድረግ ችሏል፡፡
ኢትዮጵያ ቡናና ባህር ዳር ከተማ በእንደዚህ አይነት ትልቅ ጨዋታ ሲገናኙ ለመጀመሪያ ግዜ ነው፡፡
ከመስከረም 26 እስከ ጥቅምት 10 ድረስ በተከናወነው ውድድር ቁጥሮች ምን ይላሉ
> የተመዘዙ ቀይ ካርዶች – 3
> ብዙ ቢጫ ካርዶች የተመዘዙበት – ኢትዮ-ቡና (12)
> የጨዋታ ቀናት ብዛት – 8
> በሁሉም ቀናት የታደሙ ተመልካቾች ድምር – 126,230
> በየጨዋታው የተገኘ አማካይ ተመልካች – 15,779
የውድድሩ ኮከቦችም የተመረጡ ሲሆን
ኮከብ ተጨዋች – ዳንኤል ደምሱ (ኢትዮጵያ ቡና)

ኮከብ አሰልጣኝ – ዲዲዬ ጎሜዝ (ኢትዮጵያ ቡና)

የስፖርታዊ ጨዋነት አሸናፊ – ባህር ዳር ከተማ
ምርጥ ጎል – ግርማ ዲሳሳ (ባህር ዳር ከተማ)
አስተያየት ይስጡ