መነሻ ገጽ ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ ኢትዮጵያ ቡና ከተሰፋ ቡድን 9 ተጨዋቾች ለዋናው ቡድን ለማሳደግ  መልምለዋል፡፡
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

ኢትዮጵያ ቡና ከተሰፋ ቡድን 9 ተጨዋቾች ለዋናው ቡድን ለማሳደግ  መልምለዋል፡፡

አጋራ
አጋራ

ኢትዮጵያ ቡና ከተሰፋ ቡድን 9 ተጨዋቾች ለዋናው ቡድን ለማሳደግ  መልምለዋል ክለቡ በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ገልፆል፡፡

አሰልጣኝ ድራጎን ፖፓዲች ከተስፋው ቡድን (U-20) እና ከ17 አመት በታች በአጠቃላይ 9 ተጨዋቾችን ለዋናው ቡድን የሚመጥኑ መልምለዋል፡፡

አሰለጣኝ ድራጎን የመለመሏቸውን ታዳጊ ተጨዋቾች ያሉበትን የብቃት ደረጃ ለማወቅ የኩፐር ቴስት (በአካል ውስጥ  የሚገኝ የስብ መጠን ለማወቅ፣የትንፋሽና አጠቃላይ የአካል ብቃት ምርመራ) እንዲያካሂዱ አድርገዋል፡፡

ሰኔ 20/2009 የዋናው ቡድን የልምምድ ሜዳ ላይ ተገኝተው ለታደጊዎቹ በዘመናዊ መሳሪያ በታገዘ ምርመራውን ያደረጉላቸው ታዋቂዉ የኤክሰርሳይስ ፊዝዮሎጅስቱ (exercise physiologist) ደ/ር ኤልያስ አቡሸክር ናቸው፡፡ የምርመራ ዉጤታቸው በቅርብ የሚታወቅ ሲሆን አሰልጣኝ ድራጎን ገና ከአሁኑ በታዳጊዎቹ አጠቃላይ እንቅስቃሴ እና ብቃት መደሰታቸው እንዲሁም ተስፋ ያለቸዉ ተዳጊዎች እንዳገኙ ገልፀዋል፡፡ 8ቱ ከተስፋው ቡድን (U-20 ) የተመለመሉት ታዳጊ ተጨዋቾች


  1. ዳግማዊ  ብስራት —– የመሃል ተከላካይ

  2. ጥላሁን ካሳሁን——– የመሃል ተከላካይ

  3. አብዱልባሲጥ ከማል—– የተከላካይ አማካይ

  4. አቡበከር ሻሚል———— መሀል /ሚድፊልደር 

  5. አሚር እንድሪስ———– መሀል /ሚድፊልደር

  6. አዲስ ፍስሀ—————– መሀል /ሚድፊልደር

  7. ታምራት በቀለ————- መስመር አጥቂ

  8. ኪሩቤል ይጥና———— መስመር አጥቂ 

ሲሆኑ ከ17 ዓመት በታች የተመረጠው  

  9. ቅዱስ ተስፋዬ—— አጥቂ 

ከታዳጊ ተጨዋቾች በተጨማሪ የዋናው ቡድን ተጨዋቾችም የኩፐር ቴስት ምርመራዉን ያደረጉ ሲሆን ዉጤቱም በቅርብ ዶክተሩ እንደሚያሳዉቁ ይጠበቃል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜና እረፍትዜናዎች

የጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ አጭር የህይወት ታሪክ

ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ከእናቱ ከወ/ሮ ጌጤ ገ/ስላሴ እና ከአባቱ ሀምሳ አለቃ ወልዴ...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜናዎች

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...