ኢትዮጵያዊያኖቹ ተጫዋቾች በግብፅ !

 

በግብፅ የሚገኙት የዋልያዎቹ ተጫዋቾች ሽመልስ በቀለ እና ኡመዱ ኡክሪ የግብፅ ሊግ ዳግም በዚህ ሳምንት መጀመሩን ተከትሎ በመጪው ዕሁድ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ ።

አል መካሳ ከ አስዋን ጋር የሚያገናቸው ይህ መርሐ ግብር በጉጉት ሲጠበቅ በተለይም የሽመልስ በቀለ ቡድን አል መካሳ 17ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ በወራጅ ቀጠናው መገኘቱን ተከትሎ ብርቱ ፉክክር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል ።

የኡመድ ኡክሪው አስዋን ክለብ ከተጋጣሚው አል መካሳ ክለብ በአራት ነጥቦች ብቻ እርቀው በ 13ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ ።

ይህ ተጠባቂ መርሀ ግብር እሁድ አመሻሹን 11:00 ሰዓት ጀምሮ መካሄዱን ሲጀምር በተለይም ኡመድ ኡክሪ ሙሉ ለሙሉ ከጉዳቱ በማገገም የሚሰለፍ ከሆነ በኢትዮጵያውያን ተጫዋቾች መካከል ትልቅ ፍክክር እንደሚታይ ይጠበቃል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor