መነሻ ገጽ ሀዋሳ ከተማ ​ሪፖርት | አዳማ ከተማ በሜዳው ሀይቆቹን በማሸነፍ ጣፋጭ 3ነጥብ ማግኘት ችሏል
ሀዋሳ ከተማሪፖርትአዳማ ከተማ

​ሪፖርት | አዳማ ከተማ በሜዳው ሀይቆቹን በማሸነፍ ጣፋጭ 3ነጥብ ማግኘት ችሏል

አጋራ
አጋራ

በኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ 5ኛ ሳምንት ጨዋታ ሀይቆቹን ያስተናገዱት አዳማ ከተማዎች በኤፍሬም ዘካሪያስ ብቸኛ ጎል ሀዋሳ ከተማን መርታት ችለዋል፡፡
የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ክልል ላይ ከተደረጉት ጨዋታዎች ቀደም ብሎ 08:57 ደቂቃ ላይ ነበር የተጀመረው  በጨዋታው የመጀመሪያውን 5 ደቂቃዎች ከሁለቱም ቡድኖች ከመስመር እየተነሱ እሚጣሉ ኳሶች አደጋ ይፈጥሩ ነበር፡፡

በ14ኛ ደቂቃ ላይ ሀይቆቹ  ላውረንስ ላርቴ በወንድማገኝ ማዕረግ በጉዳት ምክኒያት ለመቀየር ሲገደዱ በተቃራኒው አዳማዎች ከ1 ደቂቃ በኃላ  በጉዳት ምክኒያት  ቡልቻ ሹራን በበረከት ደስታ ቀይረው ማስገባት ችለዋል፡፡
19ኛ ደቂቃ ላይ ሱራፌል ዳኛቸው ከመሀል ክፍል ለሱልይማን የሰነጠቀለት ኳስ ከበረኛው ሜንሳህ ጋር ተገናኝቷ ኮርና ስትወጣ ከኮርና የተሻማችውን ኳስ ኤፍሬም ዘካሪያስ የቀድሞ ክለቡ ላይ በግንባር ገጭቶ ማስቆጠር ችሏል፡፡

 

በመጀመሪያው የጨዋታ አጋማሽ ግጭት የበዛበት እና መሀል እና መስመር ላይ ከሚነሱ ኳሶች ሁለቱም ቡድኖች በተደጋጋሚ ወደ ጎል መድረስ ችለዋል ሀዋሳ ከተማዎች ተጭነው በመጫወት የተሻሉ ነበሩ፡፡

በሁለተኛው የጨዋታ ክፍለ ግዜ  በተጀመረባቸው ደቂቃዎች ሀዋሳዎች ይበልጥ ተጭነው ለመጫወት ሲሞክሩ የተሻለ የኳስ ፈሰትንም ለማድረግ ችለዋል፡፡ 

በ59ኛ ደቂቃ ላይ ጋብሬኤል መሀመድ መሀል ላይ የተገኝችውን ቅጣት ምት  በጥሩ ሁኔታ ከመረብ አሳረፋት ሲባል ጃኮ ፔንዜ በግሩም ሁኔታ አድኗታል፡፡
ከጎልዋ ሙከራ በኃላ አዳማዎች በመጠኑ አፈግፈግው ሲጫወቱ አልፎ አልፎ እሚያገኟቸውን አጋጣሚዎች በመጠቀም ረገድ የተሻሉ ነበሩ፡፡
 በዚሁ ጨዋታው በአዳማ 1-0 አሸናፊነት ሲጠናቀቅ ከሜዳው ወጪ ነጥብ መሰብሰቡን ያለቻለው የአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ሀዋሳ ከተማ ነጥብ ሳይዝ ለመመለስ ተገዷል፡፡
የአሰልጣኞች አስተያየት 

ምክትል አሰልጣኝ አስቻለው ሀይለሚካኤል ~አዳማ ከተማ

” የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ተመጣጣኝ ነበር። ያገኘውን የግብ ዕድል ተጠቅመን ሶስት ነጥብ ይዘን መውጣት ችለናል። ለመሸናነፍ በነበረው ትግልም ጨዋታው ትንሽ ሀይል የቀላቀለ ነበር። በቡድናችን ውስጥ በርካታ ተጨዋቾች በአማካይ እና አጥቂ ክፍል ላይ ተጎድተውብናል።”

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ~ ሀዋሳ ከተማ

” በጨዋታው ላይ የመሀል ተከላካያችን በጉዳት ከሜዳ ወጥቶ ወደ ሆስፒታል ሄዷል። ከዚህ በኃላ ከጨዋታው ይልቅ ግጭቶች በርክተው ነበር፡፡ ጨዋታውን ለመቆጣጠር ጥረት አድርገናል። ከዛ ውጪ የቆሙ ኳሶችን በመከላከሉ ረገድ ድክመት ነበረብን። የተቆጠረብን ጎልም የገባው ከቆመ ኳስ የተነሳ ነበር። ከዚህ ውጪ ቡድኔ ከእስካሁኑ የተሻለ ለመንቀሳቀስ ሞክሯል። “


አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
አዳማ ከተማዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

አዳማ ከተማ እና አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ተለያዩ

አዳማ ከተማ ባደረገው ስብሰባ ዋና አሰልጣኙን ከክለቡ አሰናብቷል። በክረምቱ የዝውውር መስኮት በርከት...

ሀዋሳ ከተማዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዝውውር ዜናዎች

ሀዋሳ ከተማ ወጣቱን የቀድሞው የግብ ዘቡን አስፈረመ

ኢትዮጵያ ቡና ቢሮ ገብቶ በድንገት ለሀዋሳ የፈረመው ግብ ጠባቂ። በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ...

ሀዋሳ ከተማዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዝውውር ዜናዎች

ሀዋሳ ከተማ ሁለገቡን ተጫዋች አስፈረመ

  ከሸገር ከተማ ጋር የተለያየው አድናን ረሻድ ሀዋሳ ከተማን ተቀላቀለ። በጅማ አባጅፋር...