ኣዲስ መጪዎቹ ዋልቭስ የ ጌታነህ ከበደ ፈላጊ ሆነዋል
በያዝነው ዓመት ከቻምፒዮንስ ሺፕ ፕሪመርሊግን የተቀላቀሉት ዎልቭስ የ ደደቢቱ ኣጥቂ ጌታነህ ሁኔታ መልማዮቹ በመላክ እያጠኑት መሆኑን ኣይፋትቦል ዘግቧል።
በዘገባው ከዎልቭስ በተጨማሪ የፈረንሳዩ ሊልና እና የስፔኑ ሪያል ሶሲዳድ በኢትዮጵያዊዉ ግብ ኣዳኝ ፍላጎት እንዳሳዩ ይገልፃል።
ጌታነህ በደቡብ ኣፍሪካ ቆይታው በ ቢድቬትስ እና ፒሪቶርያ(ውሰት) ተጫውቷል። በደቡብ ኣፍሪካ በሁሉም ውድድሮች በተሰለፈባቸው 56 ጨዋታዎች 13 ጎልና 7 ጎል የሆኑ ኳሶችን ማቀበል ችሏል።
በያዝነው ዓመት የኢትዮጵያ ፕሪመርሊግ 11 ጎሎችን ያስቆጠረው ጌታነህ ኣምና ወደ ፓርቹጋል ሁለተኛ ዲቪዝዮን ሊያረገው የነበረ ዝውውር በተለያዩ ምክንያቶች መሰናከሉ ሚትታወስ ነው።
Source-https://www.eyefootball.com/mobile/37531/Wolves-monitoring-Ethiopian-star-Getaneh-Kebede.html
አስተያየት ይስጡ