መነሻ ገጽ ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ አዲሱ የዋልያዎቹ ዋና አሰልጣኝ ከሌቦች ዝርፊያ አመለጡ፤ሌባውን ለመያዝ የሮጡት አሰልጣኝ ጉዳት አጋጥሟቸው ህክምናቸውን እየተከታተሉ ነው
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

አዲሱ የዋልያዎቹ ዋና አሰልጣኝ ከሌቦች ዝርፊያ አመለጡ፤ሌባውን ለመያዝ የሮጡት አሰልጣኝ ጉዳት አጋጥሟቸው ህክምናቸውን እየተከታተሉ ነው

አጋራ
አጋራ

አዲሱ የዋልያዎቹ ዋና አሰልጣኝ ሆነው የተመረጡትና ነገ ከቀኑ በ 10 ሠዓት በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል በይፋ የኮንትራት ስምምነት እና የውል ስምምነታቸውን በፊርማቸው ለማረጋገጥ ቀጠሮ የያዙት አሸናፊ በቀለ ከተቃጣባቸው የዝርፍያ አደጋ አመለጡ።አሰልጣኙ የዝርፊያ አደጋ የተቃጣባቸው በመኖሪያ ቤታቸው በር ላይ ሲሆን ዘራፊዎቹ የአካባቢውን ጭር የማለት አጋጣሚን በመጠቀም የዋልያዎቹን አሰልጣኝ መኪና ላይ ዝርፊያ የተፈፀመባቸው ሲሆን ሌቦቹ ዝርፊያውን ፈፅመው ሊያመልጡ ሲል አሰልጣኙ ደርሰው ሌባውን አራሩጠው መያዛቸውና ሌባው በአሁን ሰዓት በህግ ጥላ ስር እንደሚገኝና ጉዳዩም በህግ አግባብ እየታየ እንደሆነ ለአሰልጣኙ ቅርበት ያላቸው ወገኖች በተለይ ለሀትሪክ ድረ-ገፅ የገለፁት። የዜና ምንጮቻችን ጨምረው እንደገለፁት አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ሌባውን ሮጠው በመያዝ ንብረታቸውን ከዘረፉ ቢያድኑትም በአካላቸው ላይ ማለትም በወገባቸው ላይ የመቀጨት አደጋ እንዳጋጠማቸው የጠቆሙት ምንጮች አሰልጣኙ በአጋጠማቸው የመቀጨት ጉዳት ምክንያት ህክምናቸውን በአመለሸጋው ፊዚዮቴራፒስት ይስሃቅ ሽፈራው ጋ በመመላለስ እየተከታተሉ መሆኑ ታውቋል።በወር 100ሺ ደመወዝ የሚቆረጥላቸው አዲሱ የዋልያዎቹ አለቃ ከዘረፉ ከተረፉ ከቀናት በሃላ በነገው ዕለት የሚዲያ ሰዎች ፊት ቀርበው መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜና እረፍትዜናዎች

የጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ አጭር የህይወት ታሪክ

ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ከእናቱ ከወ/ሮ ጌጤ ገ/ስላሴ እና ከአባቱ ሀምሳ አለቃ ወልዴ...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜናዎች

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...