አክሊሉ ዋለልኝ ቢጫ ለባሾቹን ተቀላቅሏል

 

በግማሽ ዓመቱ የተጨዋቾች መስኮት ዝውውር ላይ በንቃት እየተሳተፋ ሚገኙት ወልዋሎዎች አክሊሉ ዋለኝንን ከስሑል ሽረ አስፈረሙ።

በያዝነው ውድድር ዓመት መጀመርያ ላይ ስሑል ሽረን ተቀላቅሎ ከክለቡ ጋር የግማሽ ዓመት ቆይታ ያደረገው የቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ፣መከላከያ፣ኢትዮጵያ ቡና፣ጅማ ኣባጅፋር እና የኢትዮጲያ ከ20 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን ተጫዋች ኣክሊሉ ዋለልኝ ወልዋሎ መቀላቀሉን ተከትሎ የክረምቱ ፈራሚዎቻቸው ቁጥር ወደ 5 ከፍ አድርጎታል።

በ6 ወር የስሑል ሽረ ቆይታው ብዙ ጨዋታዎችን በአሰልጣኙ ምርጫና በጉዳት ያልተሰለፈው አማካዩ መሀል ላይ ክፍተቶች ለሚስተዋልበት ወልዋሎ ጥሩ አማራጭ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል።

Hatricksport website writer

Twitter

ዳዊት ብርሀነ

Hatricksport website writer