አትሌት ሙክታር እድሪስ ስለ ሀዋሳ ግማሽ ማራቶን ይናገራል

 

በሀዋሳ በተደረገው የታል ግማሽ ማራቶን ሩጫ የክብር እንግዳ የነበረው የ5000ሜ የአለም አሸናፊው አትሌት ሙክታር እድሪስ ከውድድሩ መጠናቀቅ በኋላ ውድድሩን በተመለከተ የሚከተለውን ብለዋል።

“በዛሬው ውድድር የተለየ ነገር ነው ያየሁት ምክንያቱም ታላቁ ሩጫ አዲስ አበባ ላይ ብቻ ነበር ከዚህ ቀደም ሲደረግ ማውቀው አሁን ግን ሀዋሳ ላይ መደረጉ በጣም አስደስቶኛል። ከሀዋሳ የወጣሁት የዛሬ 10 አመት ነበር። እኔም ለክልል በምሮጥበት ስአት እዚህ ነበርኩ።ከሶስት አመት በፊት በድጋሚ ወደ ሀዋሳ የመምጣቱ አጋጣሚ ነበረኝ ግን ለሽልማት ስለነበር የመጣሁት ደርሶ መልስ ያደረኩት እና ይህን ነገር ማየቴ አስደስቶኛል። ሀዋሳ ደግሞ ለ21ኪሜ አመቺ ናት ምክንያቱም ለአለም 21 ኪሜ ሚኒማም ስአት የሚመዘገብበት ቦታ ስለሆነ። በቀጣይነትም ከሌሎች ሀገራት የመወዳደሪያ ቦታዎች ጋር ከተማዋ ስለምትመሳሰል በትኩረት መሰራት አለበት ብሏል “።

Managing Editor at Hatricksport Website

FacebookTwitterGoogle+YouTube

ሙሴ ግርማይ

Managing Editor at Hatricksport Website