በጣም የሚወዷት እና ሁሌም የሚያነቧት ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣዎ ነገ ለገበያ ትቀርባለች።

በጣም የሚወዷት እና ሁሌም የሚያነቧት ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣዎ ነገ ለገበያ ትቀርባለች።

ሀትሪክ በነገው እትሟ ምንን ታስነብቦት ይሆን?
በሀገር ውስጥ ዘገባ የስፖርቱ ባለውለተኞችን የተነጠቅንበት ጥቁር ሣምንት ነበርና
የእሸቴ ገበየሁ “ኳስ ፊደሉ” ህልፈት ብዙዎቹን ስላሳዘነበት በአትሌትክሱ መንደር ታላላቅ ድሎችን ለማስመዝገብ እየተንደረደረ የነበረውና በተለያዩ አለም አቀፍ ውድድሮች በአጭር ርቀት ሀገሩን በመወከል ባንዲራዋ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ሲተጋ ስለነበረው አትሌት አባዲ ገና በለጋ እድሜው በድንገት በሞት ስለመነጠቃችን እንደዚሁም በተጫዋችነትና በመከላከያ እግር ኳስ ክለብ ውስጥ በቴክኒክ ዳይሬክተርነትና በተለያየ ኃላፊነቶች በመስራት የሚታወቀው ዋስይሁን ማሞ በተመሳሳይ በሞት የተለየን ስለመሆኑ መሪር ሀዘን ተሰምቶን ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጆቻቸው መፅናናትን በመመኘት ዘገባን ሰርተናል።
ሀትሪክ በሌላ የሀገር ውስጥ ዘገባዋ
“ጠንክረህ ስራ እንጂ ከሜዳ ውጪም ማሸነፍ ይቻላል፤ መሪነታችንን አሁንም አጠናክረን እንቀጥልበታለን” ያለውን የቅዱስ ጊዮርጊሱን
ደስታ ደሙንም አቅርቦላታለች።
ሌላው ከፍተኛ ተወዳጅነት ባተረፈላት THE BIG INTERVIEW በሚለው አምዷም የአዳማ ከተማው ዳዋ ሁቴሳ
“ከሁሉም ጨዋታ ቀላሉ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር የምናደርገው ነው……..“እኛ እየተጫወትንበት ያለው የአዳማ ማሊያ ሳይቀየር ዘንድሮ 5ኛ አመቱን ይዟል ስለማለቱና የአዳማን ማሊያን ባደረግኩበት አራት አመታት በቅዱስ ጊዮርጊስ ስላለመሸነፋቸው ይናገራል።
ሀትሪክ በባህር ማዶ ዘገባዋም የሊቨርፑል የስኬት ሚስጥር ተጨዋች ስለሆነው ፋብያኖን አስመልክቶና ብራዚላዊው ኔይማር ስለ ቡድኑ አጋር እና ተጨዋች ምባፔ ምርጥ ብቃት ስለመናገሩ እንደዚሁም ሌሎች ዘገባዎች አሏት። ያንብቧት። የፊት ለፊት ገጿም ይህንን ይመስላል።

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team