አስተያየት | ስሑል ሽረ 0-0 ሀዲያ ሆሳዕና

“የዛሬው ጨዋታ ደካማ እንቅስቃሴ ያሳየንበት ነበር”

ምክትል አሰልጣኝ መብራህቶም ፍስሀ(ስሑል ሽረ)

“ክለባችን መሻሻል ይፈልጋል ዝምብለህ ስር ነቀል ሳይሆን ጥገና ነው ሚያስፈልገው”

ፀጋይ ኪዳነማርያም (ሀድያ ሆሳእና)


 

ምክትል አሰልጣኝ መብራህቶም ፍስሀ

ስለ ጨዋታው

“የዛሬው ጨዋታ ደካማ እንቅስቃሴ ያሳየንበት ነበር ምክንያቱም የኛ ተጨዋቾች ሙለ ዘጠና ደቂቃ ጫና ውስጥ ነበሩ፣ከነ ጉዳታቸው የገቡ ነበሩ፣በቅጣት እና በጉዳት ያጣናቸው ተጨዋቾች ነበሩ።በረኛችን ሳናስበው በጉዳት መቀየራችን ቅያሬዎቻችንን አበላሽቶብናል።ሀድያዎች ጥሩ ተከላክለዋል፤ታክቲካል ጥሩ ስለነበሩ እንደ ሌላው ጊዜ ብዙ እድሎችን መፍጠር አልቻልንም።ተከላክለው ለመውጣት ሚመጡትን ቡድኖች እንዴት ማስከፈት አንዳለብን ለቀጣይ ተዘጋጅተን እንመጣለን።ዛሬ ሁለት ነጥቦችን አጥተናል እነዚህን ነጥቦችን ለማካካስ ቀጣይ ባህርዳርን ለማሸነፍ ነው ምንዘጋጀው።

ፀጋይ ኪዳነማርያም(ሀድያ ሆሳዕና)

 

“እንደምታቁት ቡድኑን ከተቀላቀልኩኝ አንድ ሳምንት ነው የሆነኝ ልጆቹን ውድድር ላይ ነው ያገኘሁዋቸው አጋጣሚ ሆኖም የአሰልጣኞች ቡድን የለኝም።እዚ የነበሩት ስለለቀቁ ብቻዬን ነው ያለሁት እናም አንዳንድ ማግኘት ምፈልጋቸው መረጃዎች ማግኘት አልቻልኩም።ሆኖም ግን ፈታኝ ጊዜ ላይ ነው ቡድኑን የያዝኩት ይህንን ፈተና ለማለፍ ነው ሀላፍነት ይዤ የገባሁት።”

ቡድኑን ከወራጅነት ለማትረፍ እየተደረገ ስላለው ዝግጅት

“ቀሪውን አንድ ጨዋታ በስነልቦና ደረጃ ነው እያዘጋጀን ያለነው ተስፋ እንዳይቆርጡ ሁሉንም ጨዋታዎች እንደ ጥሎ ማለፍ እንዲያይዋቸው እያደረግን ነው።ክለባችን መሻሻል ይፈልጋል ዝምብለህ ስር ነቀል ሳይሆን ጥገና ነው ሚያስፈልገው።ሚታዩ ክፍተቶች አሉ በሁሉም ቦታዎች እነሱን ለመድፈን ጠንከር ያሉ ሊጉን ሚያቁ ተጨዋቾች ያስፈልጉናል።ልምድ ያላቸው ተጨዋቾች ያስፈልጉናል እንደምታዩዋቸው የኛ ተጨዋቾች ብዙ ልምድ የላቸውም ስለዚ በነዚህ ክፍተቶች ላይ እየሰራሁኝ ነው።”

Hatricksport website writer

Twitter

ዳዊት ብርሀነ

Hatricksport website writer