ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ ለስልጠና ወደ ሞሮኮ ያቀናሉ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ እና የካፍ ኤሊት ኢንስትራክተር የሆኑት አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ የካፍ ኤሊት ኢንሰትራክተሮች ለሚሳተፉበት ስልጠና ወደ ሞሮኮ ራባት ሰኞ የካቲት 9/2012ዓ.ም ያመራሉ፡፡ በስልጠናው የካፍ ኤሊት ኢንስትራክተሮች የሚሳተፉ ሲሆን የአፍሪካ እግር ኳስን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማምጣት የካፍ ኤሊት ኢንስትራክተሮች ድርሻ ምን መሆን መቻል አለበት በሚሉ እና በቀጣይ በሚደረጉ ተግባራቶች ላይ ያተኮረ ነው፡፡
ከዚህ ስልጠና ቀደም ብሎ የካፍ አባል ሀገራት ቴክኒካል ዳይሬክተሮች ስልጠና ካሳለፍነው ቅዳሜ ጀምሮ በመካሄድ ላይ ይገኛል፤ ኢትዮጵያም በኢንስትራክተር መኮንን ኩሩ ተወክላለች፡፡ ይህ ስልጠና ከየካቲት 07/2012 እሰከ 09/2012 በሞሮኮ ራባት በመሰጠጥ ላይ ይገኛል፡፡
ከቴክኒካል ዳይሬክተሮች ስልጠና የሚቀጥለው የካፍ ኤሊት ኢንስትራክተሮች ስልጠና ከየካቲት 10 ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት እንደሚሰጥ ካፍ በላከው ደብዳቤ አሳውቋል፡፡

Via -EFF

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor