የሁለተኛው ዙር የወንዶች ኘሪሚየር ሊግ መርሃ ግብር አካል የሆነው የ16ኛው ሳምንት የሊግ ጨዋታ መጋቢት 7 እንደሚጀመር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሺን አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሺን የውድድርና ስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ ዳይሬክትሬት ዳይሬክተር በሆኑት በአቶ ሰለሞን ገ/ስለሴ አማካኝነት ለተሳታፊ ክለቦችና ለሚመለከታቸው አካላት የሁለተኛው ዙር የሊግ ጨዋታዎች መጋቢት 7/2010 ዓ/ም እንደሚጀምር እወቁት ሲሉ በላኩት ደብዳቤ ገልፀዋል፡፡
የ16ኛው ሳምንት ጨዋታዎች መጋቢት 7 ቅዳሜ በ8:00 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲዬም ፋሲል ከተማ ከ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በሚያደርጉት ጨዋታ ሲጀምር ሌሎች ጨዋታዎች በ9:00 እና በ10:00 ሰዓት በተለያዩ ከተሞችና ስታዲየሞች ቀጥለው ይካሄዳሉ፡፡