የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድንን ዋና አሰልጣኝ ፍሬው ሀይለ ገበርኤልን ኮንትራት ማራዘሙን ታዉቋል።
አሰልጣኝ ፍሬዉ ሀይለገብኤል ቀጣዩቹን ሁለት አመታት ፍሬው በብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝነት ለመቆየት መስማማታቸው የተገለፀ ሲሆን የአሰልጣኙ ወርሀዊ ደሞዙ ላይም ማሻሻያ በማድረግ በወር 50 ሺህ ብር እንደሚከፈለዉ ተገልጿል።
ከዚህ ጋር ተያይዞም አሰልጣኝ ፍሬው ሀይለገብርኤል እግር ኳሳዊ ውድድሮች በማይኖሩበት ጊዜ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን የቴክኒክ እና ልማት ኮሚቴ ላይ እንደሚሰሩ ተገልጿል።
ብሔራዊ ቡድኑ የፊታችን ዕሁድ በአበበ ብቂላ ስታዲየም ከጋና አቻቸዉ ጋር ለ2022 የኮስታሪካዉ የአለም ዋንጫ ለማለፍ የመጀመሪያ የማጣሪያ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል።