አስተያየት | ሀድያ ሆሳዕና 1-0 ጅማ አባጅፋር

በሰላም አባዲ

👉👉 የመጨረሻ ጨዋታ ስለሆነ አጥቅተን መጫወት ነበረብን ታግለን እንደ ጥሎ ማለፍ ባህሪ ነው ወደ ሜዳ ይዘን የገባነው

👉👉 ያገኘናቸውም አጋጣሚዎች መጠቀም አልቻልንም ያው ጥሩ ጨዋታ ነው ጳውሎስ ጌታቸው (ጅማ አባጅፋር)

አስተያየት | ሀድያ ሆሳዕና 1-0 ጅማ አባጅፋር

በተጣለበት የሁለት ጨዋታ ቅጣት ምክንያት ሀዋሳ ላይ ጨዋታውን እያደረገ ያለው ሀድያ ሆሳዕና ጅማ አባጅፋርን አስተናግዶ 1-0 ካሸነፈ በኋላ የሁለቱም ቡድን አሰልጣኞች አስተያየታቸውን ሰጥተውናል።

የመጨረሻ ጨዋታ ስለሆነ አጥቅተን መጫወት ነበረብን ታግለን እንደ ጥሎ ማለፍ ባህሪ ነው ወደ ሜዳ ይዘን የገባነው ፀጋየ ኪዳነማርያም (ሀድያ ሆሳዕና)

ስለጨዋታው

ያው እኔ ቡድኑን የተረከብኩት 3 ጨዋታ ሲቀረው ነው። ተጫዋቾቻችን አእምሮ ውስጥ የነጥብ ድምር ስለገቡ ትንሽ አጨራረስ ላይ ችግር ነበረብን ከዛ በመቀጠል ግን ከሜዳችን ውጪ ሂደን የታክቲክ ስራዎች ሰርተን የቡድኑ ስነልቦና መመለስ ስለነበረብን ከሜዳችን ውጪ 3ነጥብ እንዳናጣ ብየ የጥንቃቄ ጨዋታ ተጫውተን ኣቻ አርገን ወጥተናል። የመጨረሻ ጨዋታ ስለሆነ አጥቅተን መጫወት ነበረብን ታግለን እንደ ጥሎ ማለፍ ባህሪ ነው ወደ ሜዳ ይዘን የገባነው። ተጨዋቾቻችን እንዳያያቹሀቸው ቡዙ ጉጉት አለ የውጫዊ ጫና አለ አንደኛ ዙር በሜዳችን ላለመሸነፍ በሚለው ትኩረት ከፍተኛ ጥንቃቄ የተሞላበት ጨዋታ አድርገን ያው አሸንፈናል። ከምንም የበለጠ የዛሬ ጨዋታ 3ነጥብ በማግኘታችን ሁሉም ነገር ሙሉ ነበር እንዳንልም ሜዳ ላይ የነበረው እንደ ውጤት አስፈላጊ እና ወሳኝ 3 ነጥብ ስላገኘን በተለይ በተለይ ተጨዋቾቻችን ሜዳቸው ላይ ያደረጉት ተጋድሎ ደጋፊያችን ከሃድያ መጥቶ ለደገፈን ደጋፊ እና ሓዋሳ ውስጥ የሚኘው በሙሉ ደጋፊ ያደረገልን ላመሰግን እወዳለው።

ያገኘናቸውም አጋጣሚዎች መጠቀም አልቻልንም ያው ጥሩ ጨዋታ ነው ጳውሎስ ጌታቸው (ጅማ አባጅፋር)

ስለጨዋታው

ጨዋታው እንደተመለከታችሁት ነው። እንደዚህ አይነት ክስተቶች ይከሰታሉ በተለይ ከእረፍት በኃላ ሙሉ አጥቅተን ነበር። ያገኘናቸውም አጋጣሚዎች መጠቀም አልቻልንም ያው ጥሩ ጨዋታ ነው። በኔ አመለካከት መጥፎ ጨዋታ አይደለም ቡድናችን አንደኛ ልምምድ ሳይሰራ የመጣ ብድን ነው ብዙ ነገሮችን አርመን አይደለም የመጣነው ከድሬዳዋ ጨዋታ በኃላ ልምምድ ሰርቶ ነው የመጣው ሰለዚህ በአጠቃላይ ያለው ነገር እንደ እኔ እይታ ጥሩ ነው።

ስለ ፋይናንስ ችግርራቸው

እኔ እንግዲህ እንደዚህ አይነት ነገር ባትጠይቁኝ ይሻላል አንደኛ የኔ ስራ ማሰልጠን ነው። አሰልጥኜ እዚህ ጋር ያገኘኋቸውን ተጨዋቾች ጥሩ ነገር ላይ ማብቃት ነው። እንደተመለከታችሁት ቡድኑ አጥቅቶ መጫወት ይችላል ሁሉም ነገር አድርጎ የተጫወተ ቡድን ነው ተመልክታችሁታል ሰለዚህ ያንን ነገር በአመራር ላይ ያሉ ሰዎች ትቼዋለሁ እኔ መናገር አልፈልገም ።

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor