አስር የእግርኳሱ ባለውለተኞች ድጋፍ ተደረገላቸው

 

በኢትዮጲያ እግር ኳስ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽዎ ያደረጉ 10 ባለውለተኞች በዩኒየን ባርና ሬስቶራንት በተካሄደ ስነስርአት ድጋፍ ተደረገላቸው፡፡ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በሃገር ደረጃ ጉዳት እንዳያደርስ ሁሉም ወገን እየተረባረበ ሲሆን ይሄም የዚህ ርብርብ አንዱ አካል መሆኑ ታውቋል

አረፈአይኔ ምትኩ… መርሻ ሚደቅሳ..በሃብቱ ገ/ማርያም… ሲሳይ ተረፈ /ሞሪስ/ …ተስፋዬ ተመስገን… ቡታ አስምሮም… ተሾመ ተፈራ.. አይንሸት መንገሻ…. ሰለሞን ተስፋዬና ታሪኬ ቀጭኔ በሀገሪቱ እግር ኳስ ላይ ያደረጉትን አስተዋፅኦ ከግምት ያስገቡ አራት በጎ አድራጊዎች ድጋፍ አድርገውላቸዋል፡፡ በዚህ መሠረት 5 ሊትር ዘይት ሁለት አይነት ሳሙና 5 ኪሎ የካዎ ጄጄ ዱቄት 5 ኪሎ ሩዝ ሁለት አይነት ፓስታ 3 ኪሎ መኮሮኒ ሶፍት/ብዛት 12/ 2ሊትር ላርጎ ቲሸርትና ማክስ ለእያንዳንዳቸው ተበርክቶላቸዋል፡፡

ይህን መልካም ተግባር የፈጸሙት አቶ ሸዋረጋ ደስታ የሄሮን ኢንተርናሽናል ባለቤትና በደቡብ የቢ ጂ አይ ተወካይ አቶ ፍቅሩ ተረፈ አቶ ተመስገን ተወልደ ብርሃን /የሶቶይስ ባለቤት/ አቶ ሰለሞን መንገሻ ከአሜሪካ መሆናቸው ታውቋል፡፡

የርዳታው አስተባባሪ የሆነው አቶ ሸዋረጋ ደስታ ” ሁሉም የጎዳና ተዳዳሪዎችን ለመርዳት እየተረባረበ ነው ይሄም ደስ የሚል ተግባር ነው እኛም ደግሞ የእግርኳሱ ባለውለተኞችን ማስታወስ እንዳለብን በማሰብ ይህ በጎ ተግባር ፈጽመናል በዚህም ደስተኞች ነን ኮሮና ቫይረስ እስኪጠፋ ድረስ የምንችለውን ድጋፍ እናደርጋለን አብረውኝ የነበሩ አጋሮቼን አመሠግናለሁ ብሏል፡፡ ርዳታው ከተበረከተላቸው መሃል አቶ በሃብቱ ገ/ማርያም በበኩላቸው” አስታዋሽ አግኝተን ለተደረገልን ድጋፍ አመሠግናለሁ በዚህም ደስ ብሎኛል በቀጣይ ከናንተ ጎን ለመሆን የምንጠየቀውን ለማድረግ ዝግጁ ነን እግዚአብሄር ይስጥልን” በማለት ለርዳታው አመስግነዋል፡፡

አፍራካ ህብረት ከብስራት ሬዲዮ ዋና መስሪያ ቤት ከፍ ብሎ የሚገኘው ዩኒየን ባርና ሬስቶራንት ሙሉ የምግብና መጠጥ መስተንግዶውን መቻሉ ታውቋል፡፡

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport