መነሻ ገጽ ኢትዮጵያ ቡና “አሰልጣኝ ዲዲዬ ጎሜዝ ለሰው ልጅ ክብር የለውም” “የኢት.ቡና ትልቁ ችግር ከላይ ያሉት አመራሮች ናቸው” አክሊሉ ዋለልኝ /የቀድሞ የኢት.ቡና ተጨዋች/
ኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

“አሰልጣኝ ዲዲዬ ጎሜዝ ለሰው ልጅ ክብር የለውም” “የኢት.ቡና ትልቁ ችግር ከላይ ያሉት አመራሮች ናቸው” አክሊሉ ዋለልኝ /የቀድሞ የኢት.ቡና ተጨዋች/

አጋራ
አጋራ

በዮሴፍ ከፈለኝ

ሀትሪክ፡- የሀዋሳ ልጅ ነህና…
እነማንን አርአያ አድርገህ እያየህ አደግክ?

አክሊሉ፡- በልጅነቴ እነ ሙሉጌታ
ምህረት… አዳነ ግርማን እያየሁ ነው
ያደኩት አብዛኛው ጊዜ የስፖርት
ማዘውተሪያ ስፍራ እንደመኖሩ በአካባቢዬ
ኳስ እየተጫወትኩ ለማደግ ችያለው፡፡ ኳስ
ተጨዋች ለመሆን ያልተቸገርኩትም ለዚህ
ነው፡፡

ሀትሪክ፡- እስካሁን የት የት ክለብ
ተጫውተሃል?

አክሊሉ፡- የመጀመሪያ መነሻ የሆነኝ
የሀዋሳ ቢ ነው ከዚያ በቀጥታ ወደ ዋናው
ቡድን አደኩኝ፡፡ ከዚያ ባለፉት 3 አመታት
ለቡና ተጫውቼ አሁን ለ2ዐ11 ወደ ጅማ
አባጅፋር አቅንቻለሁ፡፡

ሀትሪክ፡- ከዲዲዬ ጎሜዝ ወደ
ዘማሪያም ተዛውረሃል ማለት ይቻላል…
ልምምድ ጀመራችሁ?

አክሊሉ፡- ገና ከቡድኑ ጋር አልተቀ
ላቀልኩም መቼ እንደሚጀመርም አልታወ
ቀም፡፡

ሀትሪክ፡- ለጅማ የፈረምከው
በሻምፒዮንስ ሊግ ለመጫወት? ወይስ
ገንዘቡ ተመችቶህ?

አክሊሉ፡- (ሳቅ በሳቅ) አይደለም፡
፡ ሻምፒዮን ቡድንም ነው በተጨማሪም
በአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮንስ ሊግ ኢትዮጵያን
የሚወክል ክለብ ነው፤ በዚያ ላይ ቡና ላይ
የምወዳቸውን ተጨዋቾች አገኛለው…
ስብስቡ የተሻለ የሚባል በመሆኑ ልፈርም
ችያለው ጫና አለብን ነገር ግን በርትቶ
በርቶ ጫናን መቀነስ ይቻላል ባይ ነኝ፡፡

ሀትሪክ፡- በቡና ተሰላፊነት 3 አመት
ቆይተሃልና… ክለቡን እንዴት አገኘኸው?

አክሊሉ፡–በጣም አሪፍ የሚባሉ ነገሮች
አሉት፡፡ ትልቅ ክለብ እንደመሆኑ ሁልጊዜ
መስራት ይጠበቅብሃል፡፡ ሁሌ ለልምምድና
ለጨዋታ ዝግጁ መሆን አለብህ ለመዝናኛ
ጊዜ አይኖርም፡ ጠንካራ ሰራተኛ መሆን
ከተጨዋቹ ይጠበቃል፡፡ በርካታ ደጋፊዎች
ባለቤት በመሆኑ ለመዝናናትና ለማሸነፍ
የሚመጣን ደጋፊ ሰርቶ ማስደሰት
ይጠበቃል ቡና በጣም ትልቅ ክለብ ነው፡፡

ሀትሪክ፡- ወደ ጅማ ስትሄድ አሰልጣኘ
ዲዲዬ ጎሜዝን አልጨብጥም አልከው
አሉ… ይሄን ያህል ተከፍተህ ነበር?

አክሊሉ፡- ቡና ይፈልገኝ አይፈልገኝ
እርግጠኛ አልነበርኩም ጎሜዝ ከመምጣቱ
በፊት 2ኛ አመት ላይ እያለሁ ውል
ለማደስ ድርድር ላይ ነበርን፡፡ ያ ማለት
2ዐ1ዐ ልምምድ ሳይጀመር ነው፡፡ ጎሜዝ
ከመጣ በኋላ ደግሞ ሰብዓዊ መብቴ ላይ
መጣ፡፡ ያኔ ላቆም ወሰንኩ፡፡ እንዲህ ከሆነ
ካላከበርከኝ ካንተ ጋር ልሰራ አልፈልግም
ብዬ ተናገርኩ፡፡ የመጨረሻ ልምምዶች አካባቢ
ሞራል የሚነካ ንግግር ሲናገር ተበሳጨሁ፡
፡ ሜዳ ላይ ልምምድ ልንሰራ ስንል ጓደኞቼን
ጨብጬ እርሱን አልጨብጥም ስል
ካልጨበጥከኝ አብረኸኝ አትሰራም አለኝ፡፡
እኔም አብሬህ ልሰራ አልፈልግም ብዬ ጥዬ
ወጣው፡፡ ሰውዬው የዘረኝነት ንግግር ነበር
ሲናገር የነበረው፡፡

ሀትሪክ፡-አሰልጣኙ ለምን አላሰለፈኝም
ነው ጥያቄህ?

አክሊሉ፡-አለማሰለፍ ከወቅታዊ አቋምና
ከታክቲክ አንፃር ሊሆንይችላል ስለዚህ
አልቃወምም እኔ ላይ ብቻ ሣይሆን ሌሎችን
ጭምር ይናገራል፡፡ ያኔ ቅር ቢለኝም ዝም
ብዬ ነበር፡፡ በርግጥ ዝምታዬ አይጠበቅብኝም
ነበር፡፡ አሁን ግን እኔ ላይ መጣ፡፡ ያኔ ራሴን
መከላከል ጀመርኩ፡፡

ሀትሪክ፡- አሰልጣኝ ዲዲዬ ጎሜዝን
በሙያና በስብዕና አንፃር እንዴት አገኘኸው?
ቡድኑ ውስጥ የአንድነት መንፈስ የጠፋው
በአሰልጣኙ ነው የሚሉ አሉ… እውነት ነው?
አክሊሉ፡-እውነት ነው ስለ ጎሜዝ አንድ
ጥሩ ነገር መናገር የሚቻለው በአሰልጣኝነቱ
ነው፡፡ ልምምድ ሲያሰራን አቅም እንዳለው
ያሳያል ጉብዝናውን እመሰክራለው፡፡ ነገር
ግን ጥሩ ማሰራት ብቻውን በቂ አይደለም፡
፡ ባህሪ ወሳኝ ነው፡፡ በየሳምንቱ ቡና ጨዋታ
ካለው ስታዲየሙ መቀመጫ የለውም፡፡ ጎሜዝ
ደግሞ አቅም ቢኖረውም እንደ አሰልጣኝ
ያንን ደጋፊ ለማስደሰት የሚያስችል ዝግጅት
አያደርግም አሰልጣኝ ዲዲዬ ጎሜዝ በባህሪው
ፍፁም ለሰው ልጅ ክብር የለውም፡፡ በራሱ
ቋንቋ ይሳደባል፡፡ ከአውሮፓ እንደመምጣቱ
የምስራቅ አፍሪካ ሰዎች እንደርሱ ማሰብ
እንደማይችሉ ነው የሚያስበው፡፡ ይሄ ባህሪው
የጥንቱን ነገር እንድታስብ ነው የሚያደርገው፡
፡ ኢትዮጵያዊያንን ይንቃል ይሄን አይቻለው
ታዝቤዋለው፡፡

ሀትሪክ፡–የቡና አዛዡ ማነው? አዛዡ
በዝቷል የሚሉ ሰዎች አሉ… ይሄን
ታዝበሃል?

አክሊሉ፡-(ሳቅ) ምን ይደረግ፡፡ ችለህ መኖር
ነው የሚያስነውሩ ትዕዛዞች ትታዘዛለህ… ምን
ታደርገዋለህ ችለህ መቆየት ነው፡፡ እነዚያን
ድርጊቶች አይተን ከንፈር ከመምጠጥ ውጪ
ምንም ማድረግ አልቻለንም ይሄ አሳዝኖኛል፡፡
ሀትሪክ፡-ይሄን ችግር ለክለቡ የበላይ
አመራሮች ነግራችሁ ታውቃላችሁ?

አክሊሉ፡- እነርሱ ትክክለኛ ሃሳብና
ቅሬታ እንዲመጣ አይፈልጉም፡፡ ለኛም
ፍቅር አልሰጡንም ቅሬታችንን መናገር
እንድንችል እንኳን አላደረጉንም፡፡ በነርሱ
መንገድ በተባልነው መስመር መሄድ እንጂ
ለክለቡ የሚበጀውን መናገርና ቅሬታ ማቅረብ
አይቻልም፡፡ የራሳቸውን ነገር ተናግሮ
ከመሄድ ውጪ የተጨዋችን ህሊና የሚጎዳ
ሞራል የሚገድል ነገር አድርጎ ከመሄድ
የተሻለ ነገር አላየሁም፡፡

ሀትሪክ፡-አሰልጣኙ ምክትሎቹን
አያግዙኝም ይላል እነርሱ ደግሞ መቼ ጊዜ
ተሰጠን መች እንድንሰራ ፈቀደልን ይላሉ፡፡
የቱ ነው ትክክል… ከታዘብከው አንፃር?

አክሊሉ፡- ስለነርሱ የመናገር ግዴታ
ውስጥ አልግባ፡፡ ተገቢ ሰው አይደለሁም፡
፡ እንደ ተጨዋች ማንም ሲያሰራኝ አብሬ
እሰራለሁ፡፡ ምንም መረጃ ሳይኖራቸው
ቦታውን እንዳላገኙ አምናለው፡፡ ስለዚህ
በሁለቱም ወገኖች የመስራት ግዴታ አለብኝ
ብዬ አስባለው፡፡ ከአይን ምስክርነት አንፃር
ግን ምክትል አሰልጣኞቹ የራሣቸውን ሃሳብ
ሲሰጡትና ሲያማክሩት ጎሜዝ ፍቃደኛ
አይሆንም፡፡ እርሱን የመሰለ አስመሳይ
ፈረንጅ አለ እንዴ? ብለህ እንድትጠይቅ
ያደርግሃል፡፡ አሰልጣኙ በጣም አስመሳይ ነው፡
፡ ከመሃመድና ከሀብተወልድ ይልቅ ብዙ ጊዜ
ማግኘው ጎሜዝን ነው፡፡ የማሰልጠን እድል
አያገኙም፡፡ ምናልባት ልምምድ ከመጀመሩ
በፊት የማሟሟቅ ስራ ይሰሩ ይሆናል እንጂ
እንዲያሰለጥኑ እድል አግኝተው አያውቁም፡፡
ይሄን አይቻለው

ሀትሪክ፡- ቡና ዋንጫ ከወሰደ 7 አመት
ሞላው አሁንም እንዳይደግም መሰረታዊ
ችግሩ ምንድነው ትላለህ?

አክሊሉ፡-የኢትዮጲያ ቡና አንድና አንድ
ችግር ከላይ ያሉት አመራሮች ናቸው፡፡
አመራሮቹ ከዘመኑ ጋር ለመሄድ ከፈለጉ
አስተሳሰባቸውን መቀየር አለባቸው፡፡ በርግጥ
ነጭ ሰው ይምጣ አይምጣ ማለት ባልችልም
ነጩን አሰልጣኝ ያመጡት የነርሱን ጫና
እንዲሰራላቸው ያልሰሩትን ብዙ የቤት ስራ
እንዲሸፍንላቸው ይመስለኛል፡፡ ያልሰሩት
ብዙ ስራ ስላለ ቢሰሩም እንኳን በኋላ ቀር
መንገድ በመሆኑ ይህን ለመሸፈን ያደረጉት
ይመስለኛል፡፡ ከፍተኛ ችግር አለባቸው፡፡

ሀትሪክ፡-ከጎሜዝ ጋር ባትጋጩ በቡና
ማሊያ መቀጠል እድሉ ወይም ፍላጎቱ
ነበርህ?

አክሊሉ፡-ቡናም ፈልጎኝ እኔም ተመችቶኝ
ለመቀጠል የሚያስችል እድሉ ነበረኝ፡፡
ከጎሜዝ በፊት በነበረ ውል የማደስ ሂደት
በተለይ በክፍያ የነበረውን ልዩነት ለማጥበብ
ድርድር እያደረግን ስለነበር ውሉን የማደስ
እድሉ ነበር በኋላ ላይ ግን ጎሜዝ ሲመጣና
ከርሱ ጋር መስራት የማልችልባቸው ብዙ
ልዩነቶች ሲመጡ ሳይሳካ ቀርቷል፡፡

ሀትሪክ፡-የመስዑድ መሀመድ፣ ኤሊያስ
ማሞ፣ አስቻለው ግርማ፣ የሀሪሰንና የሳኑሚ
አለመኖር ቡናን አይጎዳም፡፡ ?

አክሊሉ፡- በደንብ አድርጎ ነው የሚጎዳው፡
፡ የነበረህን ቡድን በአንዴ አትቀይርም
የአሁኑን ቡድን ወደፊት የምናየው ይሆናል፡
፡ ኳስ ስለሆነ ሜዳ ላይ ይናገራል፡፡ ልክ ነው
አይደለም የሚለውም ጊዜው ይናገራል፡፡
አዘጋጅተህ አስናድተህ ከሆነ የስኳድ ለውጡ
ችግር ላይኖረው ይችላል፡፡ ነገር ግን እንዲህ
አይነቱ ለውጥ ግን ያሳዝናል፡፡ ለቡድኑ
የታገሉ ሰዎችን በቀላሉ ቻዎ ማለቱ ቅር
ያሰኛል ለእኔ ተሰምቶኛል፡፡

ሀትሪክ፡- ከሀሪስን ጋር ተጋጨተው
ተለያይተዋል… የፀቡ ዕለት ነበርክ?

አክሊሉ፡- በዕለቱ በቦታው ላይ
አልነበርኩም ነገር ግን ከሀሪሰን ጋር በደንብ
እናወራና ስለሰውየው ብዙ ነገር ይነግረኝ
ነበር፡፡ ማለት እናንተም የእግር ኳስ አሰልጣኝ
እንዳላችሁ እኔም አሰልጣኝ አለኝ የኔን
ችግር መናገር ካለበትም የሚችለው እርሱ
ነው ሀሪሰን አሰልጣኝ ጎሜዝ እኔን ካከበረኝ
አሰልጣኜን ማክበር አለበት ይል ነበር፡
፡ የሀሪሰን አሰልጣኝ ውበሸት ነው ሀሪሰን
ከተሳሳተ መጠየቅ ያለበት ውብሸት ነው
በሀሪሰንን ዙሪያ ውብሸት ነው ኃላፊነት
የሚወስደው የሚል አቋም ነበረው፡፡ ብዙ ጊዜ
እናወራ ነበር፡፡ ለኔ ፍቅርና ክብር ሳይሰጠኝ
ከኔ ውጤት እንዴት ይጠብቃል? ይል ነበር፡፡
አክብሮኝ ሳከብረው ውጤት ይመጣል ስራው
በፍቅር ይሰራል ይልም ነበር፡፡ እርሱ ብቻ
ከባድ፣ ሃያል ለቡና ወሳኝ መሆኑን ብቻ
ለማሳየት እየሞከረ ስኬት አይመጣም፡፡ ከሀገሬ
የመጣሁት ለስራ ነው እግር ኳስ ልጫወት
ነው የመጣሁት እኔ ፕሮፌሽናል ነኝ፤ እርሱ
ይህን አድርግ እስኪለኝ የምጠብቅ አይነት
ሰው አይደለሁም በማለት መከፋቱን ይነግረኝ
ነበር፡፡ ነገር ግን ሲጣሉ አልነበርኩም፡፡

ሀትሪክ፡-ለኢትዮጵያ ቡና አመራሮች
የምታስተላልፈው መልዕክት አለ?

አክሊሉ፡- ለአመራሮቹ ሳይሆን
ለደጋፊዎቹ ነው መናገር የምፈልገው፡
፡ አንድ ቀን ቡድኑ የዋንጫ አሽናፊ
ሆኖ እንደምትደሰቱ ተስፋ አደርጋለው፡
፡ ቡድናቸውን ሊደግፉ በዝናብ በስብሰው
በፀሐይ ደርቀው ክልል ሄደው ተደብድበው
ዋጋ ከፍለው ቡድኑ እንዲህ መሆኑ
ቢያሳዝነኝም ትክክለኛ ስራ ተሰርቶ
የሚካሱበት አመት እንደሚመጣ ተስፋ
አደርጋለው፡፡ ምርጥ ደጋፊ መሆናቸውን
እመሰክራለሁ፡፡ በነርሱ በኩል የሚችሉትን
እየሰጡ ነው እነርሱጋር ሳይሆን ችግሩ የት
እንዳለ ቦታው ላይ ያሉ ሰዎች ራሣቸው
ያውቁታል ብዬ አስባለው፡፡ ኢትዮ ቡና
በመላው አፍሪካ በደጋፊ ብቻ ሣይሆን
በውጤት መታወቅ ነበረበት፡፡ ተፎካካሪ
ቡድን እንዲሆን አመራሩ ራሱን ሊያዘጋጅ
አሰራሩን ዘመናዊ ሊያደርግ ይገባል ማለት
እችላለው፡፡

ሀትሪክ፡- ዋሊያዎቹን እንዴት
አገኘሃቸው?

አክሊሉ፡- ሄጄ አላየኋቸውም አሪፍ
ስብስብ መኖሩን አይቻለው፡፡ ጥሩ ልጆች
ተካተውበታል ውጤታማ አሠልጣኝና
ምርጥ የአሰልጣኞች ስብስብ እንዳላቸው
አይቻለውም ጥሩ ቡድን ጥሩ ውጤት
የምናይበት እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ::

ሀትሪክ፡- ከውጪ ሀገር በክለብም ሆነ
በብሔራዊ ቡድን የማን ወዳጅ ነህ?

አክሊሉ፡-በሀገር ደረጃ የጀርመን ነኝ፡፡
በክለብ ደረጃ ሪያል ማድሪድና ዩናይትድን
እደግፋለሁ

ሀትሪክ፡-ዩናይትድ….ኒውካስትል
ዩናይትድ?

አክሊሉ፡-ዌስትሃምም አለኮ (ሳቅ
በሳቅ) እኔ ግን የማን.ዩናይትድ ነኝ (ሳቅ)

ሀትሪክ፡-ከሜሲና ከሮናልዶ…. ማን
ይቅደም?

አክሊሉ፡-ክርስቲያኖ ሮናልዶን
አስቀድማለሁ ቶኒ ክሮስም ይመቸኛል

ሀትሪክ፡- የመጫወት እድል ብታገኝ
ህልሜን የማሳካው ይህን ማሊያ ስለብስ
ነው የምትለው የማንን ነው?

አክሊሉ፡-ህልሜን አሳካውኮ!
የምፈልገው ቦታማ ተጫወትኩ፡፡
ኢትዮጵያ ቡና… ለዚህ ክለብ በመጫወቴ
ትልቅ ደስታና ክብር ይሰማኛል፡፡ አሪፍ
ቆይታ ነበረኝ በለበስኩት ማሊያ ደስተኛ
ነበርኩ፡፡ አስበው ተመኝተው መግባት
ለማይችሉበት ኢትዮጵያ ቡና በመጫወቴ
ደስተኛ ነኝ ለደጋፊውም ሆነ ለቡድኑ
ትልቅ ክብር አለኝ፡፡

ሀትሪክ፡- ታዲያ ይሄን ክለብ
መልቀቅህ ጎድቶሃል?

አክሊሉ፡–ምን ጥያቄ አለው እግር
ኳስ በባህሪው ውለታ አያውቅም፡፡ ውለታ
ውያለሁ መልሱኝ እያልኩኝም አይደለም
ህይወት ይቀጥላል፡፡ አሁን ፊቴን ወደ
ጅማ ዞሬያለሁ፡፡

ሀትሪክ፡-ከኳስ ውጪ በምን ዝና
ትላለህ?

አክሊሉ፡-ፊልም ማየት ደስ ይለኛል፡፡

ሀትሪክ፡- የሀገር ውስጥ ነው ወይስ
የውጪ ፊልም?

አክሊሉ፡-የውጪ ፊልም እመርጣለሁ

ሀትሪክ፡- ከሀገር ውስጥ የወደድከው
ፊልም የትኛው ነው

አክሊሉ፡- የወደዱ ሰሞን

ሀትሪክ፡-ያን ቆንጆ የወደድክበትን
ሰሞን ታውቀዋለህ ማለት ነው?

አክሊሉ፡-(ሣቅ በሳቅ) ባላውቀው
ይገርምሃል

ሀትሪክ፡-የወደዱ ሰሞን… እልፍ
እንበልና… ፍቅረኛ አለህ? ወይስ
አገባህ?… ወለድክ?

አክሊሉ፡- አላገባሁም.. ፍቅረኛ ግን
አለኝ፡፡

ሀትሪክ፡- በጣም አመሰግናለሁ፡፡

አክሊሉ፡- ስላስተናገዳችሁኝ እኔም
አመሰግናለሁ

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...