መነሻ ገጽ አፍሪካ “አልአህሊን እንደጠበቅነው አላገኘነውም፤ አሸንፈናቸው ልናልፍ ተዘጋጅተናል”ዐወት ገብረሚካኤል /ጅማ አባጅፋር/
አፍሪካአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግዜናዎችጅማ አባጅፋር

“አልአህሊን እንደጠበቅነው አላገኘነውም፤ አሸንፈናቸው ልናልፍ ተዘጋጅተናል”ዐወት ገብረሚካኤል /ጅማ አባጅፋር/

አጋራ
አጋራ

የጅማ አባ ጅፋሩ ጠንካራው የተከላሀዐትስፍራ ተጨዋች ሀወት ገብረሚካኤል ክለባቸው
በአፍሪካ ቶታል ቻምፒዮንስ ሊግ የግብፁን
አልአህሊ በሚፋለምበት የዐርቡ የመልስ ጨዋታ
ተጋጣሚያቸውን አሸንፈው ወደ ተከታዩ ዙር
ለማለፍ እንደተዘጋጁ አስተያየቱን ለሀትሪክ
ስፖርት ጋዜጣ ሰጥቷል፡፡

ጅማ አባጅፋር በአፍሪካ የቶታል ቻምፒዮንስ
ሊግ የክለቦች ጨዋታ የመጀመሪያ ግጥሚያውን
ከአልአህሊ ጋር ዐርብ ዕለት አድርጎ 2ለ0
የተሸነፈ ቢሆንም ይህን ውጤት መቀልበስ
እንደሚቻል የቡድኑ ተጨዋቾች ጭምር
አስተያየታቸውን እየሰጡ ይገኛል፡፡

የጅማ አባ ጅፋርና የአልአህሊን የመልስ
ጨዋታ በተመለከተና ስለመጀመሪያው ግጥሚያ
ከቡድኑ ተጨዋቾች መካከል ሀወትን አናግረነው
አጠር ባለ መልኩ ምላሹን ሰጥቷል፡፡
ከግብፁ አልአህሊ ተጫውተው 2ለ0
ስለተሸነፉበት ጨዋታና ስለነበራቸው አቋም?

‘‘የአፍሪካውንና የግብፁን ታላቅ ክለብ
አልአህሊን ተፋልመን 2ለ0 የተሸነፍንበት ጨዋታ
ለእኛ ከነበረን ጥሩ እንቅስቃሴ አንፃር እንደዚሁም
በውድድሩ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ከመሳተፋችን
አኳያ ሳየው ጥሩ የሚባል ነው፤ ውጤቱ
ጨዋታውን የሚገልፀው አልነበረም፤ የዐርቡን
ግጥሚያ ያደረግነው ከዚህ ዘግይተን በመሄድና
በተጨማሪ ደግሞ የ4 ሰዓት ተጨማሪ የመኪና
ጉዞ በማድረግ ያለ ብዙ እረፍት ነው፤ ያም ሆኖ
ግን በጨዋታው ብዙ ድካም ሳይታይብን ጥሩ
ልንጫወት መቻላችን የቡድናችንን ተጨዋቾች
እንዳመሰግናቸው አድርጎኛል፤ በዐርቡ ጨዋታ
እኛ ከተጋጣሚያችን በኳስ ቁጥጥሩ የተሻልን
ነበርን፤ ሆኖም ግን በጥቃቅን ችግሮች ጎል
ገብቶብን ልንሸነፍ ችለናል”፡፡

በጨዋታው አልአህሊዎች ስለነበራቸው
አቋም?

“አልአህሊዎች ከእኛ ጋር ሲጫወቱ የነበራ
ቸው አቋም ጥሩ ሊባል የሚችል አይደለም፤
በማጥቃቱ በኩል ጫና ፈጥረው ሊጫወቱ
አልቻሉም፤ እኛ በሚገባ ተቋቁመናቸው ተጫ
ውተናልና እንደጠበቅናቸው አላገኘናቸውም”፡
ስለ ዐርቡ የመልስ ጨዋታ
“የግብፁን አልአህሊ የምንፋለምበት የዐርቡ
ጨዋታ ለእኛ በጣም ወሳኝ ነው፤ ጎሎች
የሚያስፈልጉን ስለሆነ ሙሉ 90 ደቂቃውን
አጥቅተን ነው የምንጫወተው፤ በመጀመሪያው
ግጥሚያ 2ለ0 ተሸንፈን የመጣን ቢሆንም ይህን
ውጤት ቀልብሰንና ተጋጣሚያችንን አሸንፈን
ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ ተዘጋጅተናል”፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

አዳማ ከአስር ፈረሰኞቹ ከሦስት እና ነብሮቹ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የመክፈቻ ቀን ጨዋታ አዳማ ከተማ በጎል ደምቆ ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ...

ዜናዎችየአዲስአበባ እግርኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጠዋል የተባሉት ሁለት ዳኞች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደረገ

በዮሴፍ ከፈለኝ በወልዋሎ እና ነገሌ አርሲ ጨዋታ ላይ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ ሁለት...

ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንፊፋ

ፊፋ ቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ጥሎት የነበረውን የዝውውር ዕገዳ በጊዜያዊነት አነሳ

ቅዱስ ጊዮርጊስ በአራት የቀድሞ ተጫዋቾች ቀርቦበት በነበረው ክስ በፊፋ ጥሎበት የነበረው የተጫዋቾች...

ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

ዋልያዎቹ በአሜሪካ የወዳጅነት ጨዋታን ሊያደርጉ ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ አሜሪካ ሊያመራ ነው ነገር ግን የወቅቱ የብሔራዊ ቡድኑ...