ነፃነት ገብረመድህን ምዓም አናብስቶቹን በይፋ ተቀላቅሏል

 

የነባር ተጨዋቾቻቸውን ውል በማራዘም በይፋ ወደ ዝውውር መስኮቱ የተቀላቀሉት መቐለ 70 እንደርታዎች ነፃነት ገብረመድህንን የክረምቱ የመጀመርያ ፈራሚያቸው አድርገውታል።

ባሳለፍነው የውድድር ዓመት ከስሑል ሽረ ጋር የተሳካ ጊዜ ማሳለፍ የቻለው ወጣቱ የተከላካይ አማካይ ከጋብርኤል አህመድ(ጅብሪል) መልቀቅ በኃላ ሁነኛ ተተኪ አጥተው ለነበሩት መቐለዎች ጥሩ መፍትሄ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል።ኳሶች ማጨናገፍና ለተከላካይ ክፍል ሽፋን መስጠት ላይ የተካነው ነፃነት የትውልድ ከተማው ክለብ ስሑል ሽረን ከበርካታ ዓመታት ቆይታ በኃላ ሊሰናበት ችሏል።

በተያያዘ ዜና መቐለ 70 እንደርታዎች የነባር ተጨዋቾቻቸውን ውል የማራዘም ስራቸውን በማስቀጠል የስዩም ተስፋዬ፣ዮናስ ገረመው እና አሚን ነስሩን ውል አራዝመዋል።

Hatricksport website writer

Twitter

ዳዊት ብርሀነ

Hatricksport website writer