“ተጨዋቾች ደመወዝ አይከፈላቸው አላልኩም ” ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻው

የኢትዮጲያ ፕሮፌሽናል ተጨዋቾችና ባለሙያዎች ማህበር ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻው ላይ ተቃውሞ አቀረበየኢትዮጲያ ፕሮፌሽናል ተጨዋቾችና ባለሙያዎች ማህበር ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻው ላይ ተቃውሞ አቀረበ

አሰልጣኝ ሰውነት በቲቪ 9 ላይ በሰጡት ትንተና ተጨዋቾች ከሌላው ሙያ አይለዩም መንግስት ብር የለኝም ካለ በቃ የለውም የግድ ደመወዝ መክፈል የለበትም ማለታቸውን ማህበሩ ተቃውሞታል፡፡ እንደ ማህበሩ ቅሬታ አሰልጣኙ ትላንት በክለብና በብሄራዊ ቡድን ያሰለጠኗቸውን ተጨዋቾችና የሙያ ባልደረቦቻቸውን ከግምት ያላስገባና ቅር ያሰኘ አቋም ነው ሲል ተችቷል፡፡ የአሠልጣኙ መግለጫ የፌዴሬሽኑን አቋም የማያንጸባርቅና ክለቦችን ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ የሚወስድ ነው በማለት ከሷቸዋል፡፡

በጉዳዩ ዙሪያ ለሃትሪክ ምላሽ የሰጡት ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻው ግን ተጨዋቾች ደመወዝ አይከፈላቸው አላልኩም ሲሉ ማስተባበያ ሰጥተዋል፡፡”

ተጨዋቾች ገንዘብ ማግኘት አለባቸው ነገር ግን ይሄ ወረርሽኝ ባመጣው ችግር ምክንያት እስከታች እስከ ወረዳ ያሉ ክለቦች ሁሉ አሁን ደመወዛቸው ቆሟል በላይኛውም ደረጃ እያጫወቱ ህይወታቸውን የሚመሩ ዳኞችም አሁን ክፍያቸው ቆሟል ፎቶ እያነሱ የዕለት እንጀራቸውን የሚበሉትም እነርሱም ተዘግቶባቸዋል በየሰፈሩ ያሉ ማስቲካ ሻጮችንም ጨምሮ በእግርኳሱ ዙሪያ ጥቅም የነበረው ሁሉ ቆሟል ስለዚህ መንግስት ገንዘብ ከሌለው ሁሉም መንግስት የሚሰጠውን ራሽን ተሰልፎ አየተቀበለ ቤቱ እየቆረጠመ መኖር ነው ብዬ የግሌን አስተያየት ሰጥቻለሁ ነገር ግን ተጨዋቹ ደመወዝ ማግኘት የለበትም አላልኩም ቪዲዮውን እዩና መስክሩ” ሲሉ ለሃትሪክ ድረገጽ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡


ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻው ከቴቪ 9 ጋር ካደረጉት ንግግር የተቀነጨበ 👇

📽 ©TV9

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport