መነሻ ገጽ ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ ተወዳጇ እና ሳምንታዊዋ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ እንደተለመደው ሁሉ ምርጥ ምርጥ ዘገባዎችን ይዛ ከገበያ ላይ ለመዋል መሰናዶዋና አጠናቃለች፡፡
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

ተወዳጇ እና ሳምንታዊዋ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ እንደተለመደው ሁሉ ምርጥ ምርጥ ዘገባዎችን ይዛ ከገበያ ላይ ለመዋል መሰናዶዋና አጠናቃለች፡፡

አጋራ
አጋራ

ሀትሪክ ስፖርት፤ ሀትሪክ ስፖርት፤ ሀትሪክ ስፖርት እንዳታመልጦት
ተወዳጇ እና ሳምንታዊዋ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ እንደተለመደው ሁሉ ምርጥ ምርጥ ዘገባዎችን ይዛ ከገበያ ላይ ለመዋል መሰናዶዋና አጠናቃለች፡፡
ሀትሪክ በእዚህ ሳምንት እትሟ ምን ምን ጉዳዮችን ይዛ ይሆን?
ከሀገር ውስጥ ዘ ቢግ ኢንተርቪው በሚለው አምዷ የአዳማ ከተማ፣ የኢትዮጵያ ቡና፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የሐዋሳ ከነማ፣ እና በሱዳን ሊግም አልአህሊ ሸንዲን በማሰልጠን ያለፈውና አሁን ደግሞ የፋሲል ከተማ ቡድንን እያሰለጠነ ያለው አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለጋዜጣው በእግር ኳሱ የህይወት ቆይታውና ስለ እግር ኳሱ አካባቢ ስላሉት ጉዳዮች አስተያየቱን ሰጥቷል፤ ለመሆኑ ምን ብሎ ይሆን? አሰልጣኝ ውበቱ ከሰጣቸው ቃለ-ምልልሶች መካከል “ጄኔራሎች በሙስና ከተጠየቁ አሰልጣኙንና ቡድን መሪውን መጠየቅ ምን ይከብዳል” የሚል እና “አሰልጣኞች ብቻ አይደለም ጋዜጠኞችምኮ ገንዘብ ይቀበላሉ ይባላል” በሚል ምላሽን ሰጥቷል፤ በሀትሪክ ሌላ የሀገር ውስጥ ዘገባ በሳምንቱ መጨረሻ ስለሚጀመረው እና ተቋርጦ ስለነበረው የፕሪምየር ሊግ ውድድር እንደዚሁም ደግሞ በግብፅ የፕሮፌሽናል ተጨዋችነት የሙከራ ዕድል እየተመቻቸለት ስላለው እና ከኢትዮጵያ ቡና ጋር በጉዳት ተለይቶ ስለነበረውና በአሁን ሰዓት ደግሞ በመልካም ጤንነት ላይ የሚገኘውን ወጣቱን ተጨዋች እሱባለው ጌታቸውን አናግረነው ምላሹን ሰጥቶናል፤ ሀትሪክ በባህር ማዶ ዘገባዎቿም በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግና በሌሎች ሊጎች “ዙሪያ እንደዚሁም የሚወዱት ጣፋጭ መረጃዎችን አቅርበንልዎታል፤ ሀትሪክ እንዳታመልጦት
የሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የእዚህ እትም ይህንን ይመስላል

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜና እረፍትዜናዎች

የጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ አጭር የህይወት ታሪክ

ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ከእናቱ ከወ/ሮ ጌጤ ገ/ስላሴ እና ከአባቱ ሀምሳ አለቃ ወልዴ...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜናዎች

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...