ለኢትዮዽያ ቡና ተጠባባቂ ለዋሊያዎቹ ዋነኛ ተመራጭ ግብ ጠባቂ የነበረው ተክለ ማርያም ሻንቆ/ጎሜዝ/ ከነሀሴ 1/2013 ጀምሮ የሲዳማ ቡና ለመሆን ተስማምቷል።
ግብ ጠባቂው በኢትዮዽያ ቡና እስከ ሀምሌ 30/2013 ድረስ ውል ያለው በመሆኑ ፌዴሬሽን ተገኝቶ ለሲዳማ ቡና ፊርማውን አኑሮ ህጋዊ የሚሆነው ከነሀሴ 1/2013 ጀምሮ ይሆናል።
ግብ ጠባቂው በጥር ወር ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ቋሚ ተሰላፊ ለመሆን በክለብ ደረጃ ቋሚ መሆንና ከሌሎች ግብ ጠባቂዎች ጋር መፎካከር የግድ በመሆኑ ለኢትዮዸያ ቡና ያቀረበው የቋሚ ተሰላፊነት ማረጋገጫ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ሊለቅ መቻሉ ታውቋል።
የሲዳማ ቡናው አሰልጣኝ ገብረ መድህን ሃይሌ ለጎሜዝ የቋሚ ተሰላፊ የመሆን ዋስትና መስጠቱና ተደጋጋሚ የማስፈረም ጥረቱ ተሳክቶ ለ2 አመት ለሲዳማ ቡና ለመጫወት ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
በሁለቱ ወገኖች ስምምነት መሰረት ተክለማርያም 3.5 ሚሊዮን ብር ለ2 አመት እንዲከፈለው የተስማማ ሲሆን 2.5 ሚሊየን ብሩ በቼክ መቀበሉ ታውቋል። ቀሪው 1 ሚሊዮን ብር ደግሞ በውል ዘመኑ መሰረት ለ24 ወር የሚከፋፈልና በደሞዝ መልክ የሚወስደው መሆኑ ታውቋል።
አስተያየት ይስጡ