ብሩክ ገብረአብ ለደደቢት ፈርሟል !

 

ከሳምንት በፊት ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲን እንደተቀላቀለ የተገለፀው ብሩክ ገብረአብ ከቡድኑ ጋር በመለያየት ደደቢትን መቀላቀሉ ተገልጿል።

የቀድሞ የስሑል ሽሬ የመስመር አጥቂው ከጅማ አባጅፋር በስምምነት ከተለያየ በኋላ በዚህኛው የዝውውር መስኮት ወደ ወልዋሎ አዲግራት ዩነሰቨርሲቲ ቢያመራም ከሳምንታት ቆይታ በኋላ ለክለቡ የልቀቁኝ ደብዳቤ ማስገባቱን ተከትሎ ነው ለደደቢት ፊርማውን ማኖር የቻለው ።

ደደቢት በዝውውር መስኮቱ ኪዳኔ ገ/ፃዲቅ ፤ ሲሳይ ጥበቡ ፤ ያሬድ ገ/ኪሮስ አዲስ ፈራሚዎች ሲሆኑ መድሀን ታደሰ እና ሙሉጌታ ዓንዶም ውላቸውን ያራዘሙ ተጫዋቾች መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል ::

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor