በካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ጨዋታ የፊታችን አርብ ካይሮ ላይ ሚካሄደው የዛማሌክ እና የዛምቢያው ዜስኮ ዩናይትድን ጨዋታ ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ ሊዳኙት መመረጣቸውን የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን(ካፍ) አስታውቋል።
ምድቡን ሀያሎቹ ቲፒ ማዜምቤ በ7 ነጥቦች ሲመሩ የግብፁ ሀያል ክለብ ዛማሌክ በ4 ነጥብ ይከተላል። ዛማሌክን የሚገጥሙት ዜስኮዎች በሁለት ነጥብ የምድቡ ግርጌ ላይ ተቀምጠዋል።
በምድቡ ሶስተኛ ጨዋታ ዛምቢያ ላይ አቻ የተለያዩት ሁለቱም ቡድኖች ነገ የሚያካሂዱትን ጨዋታ በ39 ዓመቱ ባምላክ ተሰማ መሪነት ግብፅ ካይሮ ስታድየም ላይ ይካሄዳል።
በዛማሌክ ና አርኤስ ቤርካን መሀከል የተካሄደውን የአምናው የካፍ ኮንፌዴሬሽን የፍፃሜ ጨዋታን መዳኘት የቻሉት ባምላክ ተሰማ ከጊዜ ወደ ጊዜ በአፍሪካ መድረክ ላይ ያላቸው ተቀባይነት እየጨመረ ሄዷል።
አስተያየት ይስጡ