በአውሮፕላን አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ሁሉ የሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የተሰማውን የሀዘን ስሜት እየገለፀ ለሟቾቹ ቤተሰቦች መፅናናትን ይመኛል፡፡
የማክሰኞ እትም ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣዎ ነገ ገበያ ላይ ትውላለች
ባለቀለሟ እና የእናንተ ምርጫ የሆነችው ተወዳጇ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በሳምንት አንድ ቀን ለንባብ የምትበቃ ሳምንታዊ ጋዜጣ ስትሆን ነገ ማክሰኞም እንደተለመደው የተለያዩ የሀገር ውስጥ እና የባህር ማዶ ዘገባዎችን ለእናንተ ይዛሎት ለመቅረብ ዝግጅቷን አጠናቃለች፡፡
ሀትሪክ በሀገር ውስጥ የነገ እትሟ ምን ምን ጉዳዮችን ይዛ ወጥታ ይሆን? ነገ ያንብቧት፡፡ በሀገር ውስጥ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ባተረፈላት THE BIG INTERVIEW አምዷ የቀድሞ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጨዋች የነበረው ሸዋረጋ ደስታ የ1990 ዎቹ ዓመተ ምህረት መጨረሻ ላይ በቀድሞ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን አመራሮች እና በክለቦች ህብረት መካከል ተፈጥሮ ስለነበረው ውዝግብ በፃፈው መፅሀፍ ዙሪያ እና የታዳጊ ወጣቶች ፕሮጀክትን በማቋቋሙ ዙሪያ የሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ኤክስኪዩቲቭ ኤዲተር እና ጋዜጠኛ የሆነው ይስሀቅ በላይ የተለያዩ ጥያቄዎችን አቅርቦለት ምላሹን ሰጥቷል፤ ሸዋረጋ ምን ብሎ ይሆን፤ ሙሉ ምላሹን ነገ ከጋዜጣው ላይ ያነቡታል፡፡
ሀትሪክ ከዛ ውጪም ሌሎች ዘገባዎችም አሏት፤ ከእነዛም መካከል የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ብሔራዊ ቡድንን አስመልክቶ ቡድኑ እያደረገ ስላለው ዝግጅት እና የፊታችን እሁድ ሳምንት ከማሊ ኦሎምፒክ ብሔራዊ ቡድን ጋር በሚኖረው ጨዋታ ዙሪያ እንደዚሁም ሌሎችን ጥያቄዎችም ለቡድኑ ተጨዋች አማኑኤል ዩሃንስ አንስተንለት የሰጠው ምላሽም በጋዜጣው ላይ ቀርቦላችኋል፡፡
ሀትሪክ በነገው እለት ሌላ ይዛሎት የቀረበችው ዘገባ በቱርክ አየር መንገድ አዘጋጅነት ስለተካሄደው ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ ሀገራትን ስላሳተፈው የቦውሊንግ ውድድርም የቱርክ አየር መንገድ ስራ አስኪያጅ የሆኑትን ሁሴይን ቶኩሌኮን በማናገር ምላሽ የሰጡበት ዘገባም አለ፡፡
ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በባህር ማዶ ዘገባዎቿም ነገ ገበያ ላይ ስትውል በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት ስለተካሄዱት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ወሳኝ ጨዋታዎችን አስመልክቶና በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ዙሪያ እንደዚሁም ደግሞ ሌሎችን መረጃዎችን ይዘን ነገ ከእናንተ ጋር ለመገናኘት ቀጠሮን ይዘናል፤ ሀትሪክ የእናንተ ናት አታምልጦት፡፡
ሀትሪክን ከሳምንታዊ ጋዜጣዋ በተጨማሪ http://www.hatricksport.com/ ድረ-ገፃችን ላይ አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉና አሁኑኑ ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ፤ የሀትሪክ ቤተሰብም ይሁኑ፡፡
የሀትሪክ ጋዜጣ የነገው የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል፡፡
አስተያየት ይስጡ