በፕርሚየር ሊጉ ቀጣይ እጣ ፈንታ ዙርያ በካፍ አካዳሚ እየተደረገ ባለው ስብሰባ የተለያዩ ሀሳቦች በመነሳት ላይ ይገኛሉ ።

 

የምክክር ሀሳቦች ከመነሳታቸው አስቀድሞ መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ ክለቦች በአሁን ሰዓት እያደረጉት ያለው የተጫዋቾች ዝውውር በሚሊዮኖች ብር እንኳ ቢያወጡ ህገ ወጥ እና በፌዴሬሽኑ ተቀባይነት የሌለው እንሆነ በአንክሮ ገልፀዋል ።

ከተነሱ የምክክር ሀሳቦች መካከል ውድድሮች እንዲጀምሩ ውሳኔን የሚያገኙ ከሆነ የተለያዩ ተግባራት ተፈፃሚነት እንደሚያገኙ ይጠበቃል ።

ከነዚህም መካከል ጨዋታዎችን በውስን ሚዲያዎች ማድረግ ፣ በ 30ኛ ደቂቃ እና 75ኛ ደቂቃ የውሀ እረፍት መኖር ፣ በዝግ ስታዲየም ውድድር ማድረግ ፣ ሁሉም ቡድን 23 ተጫዋቾች እና 10 የቴክኒክ የህክምና ባለሙያዎችን መያዝ እንዲሁም ከጤና ጋር ተጓዳኝነት ያላቸው ጉዳዮች በጉልህ እየተነሱ ይገኛሉ ።

የተለያዩ መረጃዎችን እንዲሁም ሊወሰኑ የሚችሉ ጉዳዮችን ሀትሪክ ስፖርት ጉዳዩን እየተከታተለች የምታቀርብልዎ ይሆናል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor