የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 29ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በዛሬው እለት በክልል ከተሞች ስታዲየሞች ቀጥለው ተካሂደዋል።
ጎንደር ፋሲለደስ ስታዲየም ላይ በተደረገ ጨዋታም ፋሲል ከነማ እና ኢትዮጵያ ቡና የተገናኙ ሲሆን፥ ፋሲል ከነማ ጨዋታውን 1ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
የፋሲል ከተማን የማሸነፊያ ጎልም ሀሚዝ ኪዛ በ7ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል።
በሀዋሳ ስታዲየም የተካሄደው የሀዋሳ ከተማ እና የወልዋሎ አዲግራት ጨዋታም ያለ ምንም ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።
አዳማ አበበ ቢቂላ ላይ የተደረገው የአዳማ ከተማ እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታም ያለምንም ግብ 0ለ0 በሆነ ውጤት ተጠናቋል።
በተመሳሳይ በሶዶ ስታዲየም የተደረገው የወላይታ ድቻ እና የጅማ አባጅፋር ጨዋታም 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት መጠናቀቅ ችሏል።
ድሬድዋ ላይ ደግሞ ድሬደዋ ከተማ እና አርባ ምንጭ ከተማ የተገናኙ ሲሆን፥ ጨዋታውም 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ነው የተጠናቀቀው።
በጨዋታው ላይም እንዳለ ከበደ በ16ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠራት ጎል አርባ ምንጭን መሪ አድርጋ የነበረ ቢሆንም፤ በረከት ይስሀቅ በ90+3ኛው ደቂቃ ላይ ለድሬዳዋ ያስቆጠራት ጎል ጨዋታው በአቻ ውጤት እንዲጠናቀቅ አድርጓል።
የጅማ አባጅፋር እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥብ መጣልም የፕሪምየርሊጉን ዋንጫ ማን ያነሳል የሚለው አሁንም የመጨረሻው 30ኛ ሳምንት እንዲጠበቅ አድርጓል።
ፕሪየር ሊጉን ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ጅማ አባ ጅፋር በእኩል 52 ነጥብ እና 19 ጎል 1ኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
አስተያየት ይስጡ