“በጣት የሚቆጠሩ ግለሰቦች እያደረጉ ያሉትን ዘመቻ ደርሰንበታል ” ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻው

 

ከካፍ ኮንቬሽን ጋር ተያይዞ የሀገራችን ኢንስትራክተሮች ያላቸው ደረጃ ምን ይመስላል በሚል መግለጫው መጠራቱ ታውቋል፡፡

“ይሄ መግለጫ ያስፈለገው ውዥንብር በመፍጠር እንዳይሰሩ እየተደረገ በመሆኑ ነው ። ሁሉም ኢንስትራክተር ከካፍም ሆነ ከፌዴሬሽኑ ገንዘብ አይወስዱም” በማለት የተናገሩት ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻው “እውቀታችን ተፈትኖ ያለፍን አቅም ያለን ባለሙያዎች ነን” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

“ካፍ የማንንም ሀገር ላይሰንስ አላደሰም ይሄ ውሸት ነው፡፡ ገንዘብ የማይከፈለውን የራሱን አውጥቶ የሚሰራ ባለሙያ ሚዲያው ሊጠብቅልን ይገባል ። ከውጪ ተጨዋቹን ለማሳመጽ የሚደረግ ሙከራ አለ ፣ በጥቂት ግለሰቦች የሚደረግ ዘመቻ በተመለከተ መረጃው አለን ይህን ጉዳይ ለማስቆም በዚህ መግለጫ ብቻ አንቆምም” ሲሉ ሀሳባቸውን ሰጥተዋል ፡፡

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport