በኮቪድ 19 የተያዙት 5 ተጨዋቾች በድጋሚ ሳይመረመሩ ቀሩ

በኮቪድ 19 የተያዙት 5 ተጨዋቾች
በድጋሚ ሳይመረመሩ ቀሩ

*…ካሉበት ሆሊዴይ ሆቴል እንዲወጡ ታዟል…

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አምስቱ ተጨዋቾችን የድጋሚ ምርመራ አድርጎ ነጻ ከሆኑ ወደ ዋሊያዎቹ ስብስብ ለመመለስ የነበረው ዕቅድ ሳይሳካ ቀርቷል፡፡
የህብረተሰብ ጤና ሳይንስ ኢንስቲትዩት ኮቪድ 19 ለመከላከል የተቀመጠውን ፕሮቶኮል መጣስ አይቻልም ተጨዋቾቹ ሆቴል መቀመጥ አልነበረባቸውም የድጋሚ ምርመራ ካስፈለገ ተጨዋቾቹ ከሆቴል ወጥተው የኳራንታይን ማዕከል ወይም ገስት ሀውስ መግባት አለባቸው በማለቱ ተጨዋቾቹን በነገው ዕለት ከሆሊዴይ ሆቴል በማውጣት ለቀናቶች ወደ ገስት ሀውስ እንዲወሰዱ የፌዴሬሽኑ የህክምና ኮሚቴም ወስኗል፡፡

ተጨዋቾቹም በነገው ዕለት ከሆቴሉ ወጥተው የፊታችን ማክሰኞ የድጋሚ ምርመራ እንዲደረግላቸው መታቀዱ ታውቋል፡፡ ብሄራዊ ቡድኑን በቶሎ እንዲቀላቀሉ ለማድረግ ፌዴሬሽኑ ያደረገው ሙከራ በህብረተሰብ ጤና ሳይንስ ኢንስቲትዩት ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል፡፡ ዋሊያዎቹን በቀጣዮቹ ሳምንት ወደ ባህርዳር ለመውሰድ የነበረውን ዕቅድ እንዳያስተጓጉል ተሰግቷል፡፡

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport